Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
አለም አቀፍ ትንታኔ

ቻይና የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት 400 የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን ለኢራን ልትልክ ነው

BS Bethelhem Solomon Jul 30, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 25 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ቻይና የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት 400 የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን ለኢራን ልትልክ ነው

70 ሚሊዮን ዶላር የሚገመተው ይህ ስምምነት ቴህራን ከአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት በኋላ የአጭር ርቀት አየር መከላከያዋን ለማጠናከር የምታደርገውን ጥረት የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቁሟል።


ቻይና
የአካባቢውን አቅርቦት ለማጠናከር  400 የትከሻ ፀረ-አውሮፕላን ሮኬት ማስወንጨፊያዎችን ለኢራን ልትልክ መሆኑን የውጭ መገናኛ ብዙኃን በሰፊው ዘግበዋል።

የቤጂንግ መንግሥት ውንጀላውን ሙሉ በሙሉ መሰረተ ቢስ በማለት በጥብቅ ቢክደውም ይህ 70 ሚሊዮን ዶላር ሚስጥራዊ ስምምነት በቻይና ፕሬዚዳንት ጂንፒንግ እና በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መካከል ያለውን ግንኙነት ከፍተኛ ፈተና ውስጥ እንደሚከተው ተመላክቷል።

በሆንግ ኮንግ በሚገኘው ዞንግቺንግ ባኦሻንግ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት የተባለ አማካሪ ድርጅት በኩል የተፈረመው ይህ ውል QW-12 እና FN-16 ዓይነት የትከሻ ፀረ-አውሮፕላን ሚሳይሎችን ያካተተ ነው ተብሏል


እነዚህ በነጠላ ግለሰብ ሊሸከሙ የሚችሉ ኃይለኛ መሳሪያዎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ ግዢ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ከተጀመረው ጦርነት ወዲህ የአጭር ርቀት የአየር መከላከያ አቅሟን እና የጦር መሳሪያ ኪሳራዋን ለመተካት ካደረቻቸው ትላልቅ እና ታሪካዊ ጥረቶች አንዱ እንደሆነ ተነግሯል።


የአሜሪካ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ቻይና ከዚህ ቀደም ለባለስቲክ ሚሳይሎች ማገዶ የሚሆኑ ኬሚካሎች እና ለድሮን ማምረቻ የሚሆኑ ወሳኝ ቁሳቁሶችን ለቴህራን ልካለች።

ቻይና ለኢራን ከምታደርገው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በተጨማሪ የኢራንን ነዳጅ በቀን 1.5 ሚሊዮን በርሜል በላይ በመግዛት ለሀገሪቱ ከፍተኛ የገንዘብ ገቢ እያስገኘችላት የሚገኝለት ሲሆን  ይህም ኢራን ጦርነቱን እንድታስቀጥል የገንዘብ አቅም እየሰጠቻት መሆኑን ያሳያል።


የነዳጅ
ገበያ ተንታኞች እንደገለጹት ቻይና በመጋቢት ወር ብቻ ከኢራን የምትገዛው የዕለት ተዕለት የውጭ ነዳጅ መጠን 1.6 ሚሊዮን በርሜል ደርሷል። ይህ አኃዝ ... 2025 ዓመታዊ አማካይ ከነበረው የቀን 1.4 ሚሊዮን በርሜል ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

ምንም እንኳ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና አቻቸው ጋር ባደረጉት የዲፕሎማሲያዊ ጉብኝትና ውይይት ጂንፒንግ ለኢራን የጦር መሳሪያ ላለመላክ ጥብቅ ቃል መግባታቸውን ይህ ትልቅ መግለጫ ነው በማለት ገልጸው የነበረ ቢሆንም አሁን የተደረሰው ሚስጥራዊ ስምምነት ግን የሁለቱን ሀገሮች መሪዎች ግንኙነት ወደ ከፉ ቀውስ ሊመራው ይችላል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ሰፊው ግጭት እየተባባሰ በሄደበት በዚህ ወቅት ሳውዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር በመሆን በኢራን ላይ ኃይለኛ ጥቃት የፈጸመች ሲሆን በሌላ በኩል ዩክሬን በካስፒያን ባህር ውስጥ የሚገኝ የኢራን የጭነት መርከብ ላይ ዒላማ አድርጋ መመታቷ ይታወሳል።


ይህ ድርጊት በኢራን እና በዩክሬን ጦርነቶች መካከል የመጀመሪያው ቀጥተኛ መተሳሰር መሆኑን የገለጹት የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንድሪ ሲቢሃ የኢራን የበቀል ዛቻዎች ምንም ዓይነት መሰረት የሌላቸው መሆናቸውን አፅንዖት ሰጥተዋል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

55 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።