Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የቤት ኪራይ ዋጋ መተመኛ ጥናት ቀረ�

BS Bethelhem Solomon Jun 26, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 553 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የቤት ኪራይ ዋጋ መተመኛ ጥናት ቀረበ

ጥናቱ ለአከራይ ፍትሃዊ ገቢን ለተከራይ ደግሞ አቅሙን ያገናዘበ የኪራይ ዋጋን በማረጋገጥ የሁለቱንም ወገን ተጠቃሚነት ያሰፍናል ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን ሳይንሳዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመምራት የተዘጋጀ መተመኛ ጥናት ለፓናል ውይይት ርቧል


የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ እና የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ መምህራን በጋራ ያከናወኑት ይህ አዲስ የዋጋ መተመኛ ጥናት ከሚቀጥለው 2019 በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ታውቋል።

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ጫናን ለመቀነስና በቤት ኪራይ ገበያው ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ህገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን ለመግታት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።


ቢሮው 2016 . ሰፊ የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባ ማከናወኑን ያስታወሱት ኃላፊዋ ይህም በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የከፈተና ያልተገቡ አሰራሮችን ያስቀረ ትልቅ ስኬት እንደነበር ገልጸዋል።

በአዋጁ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የተዘጋጀው ይህ የዋጋ መተመኛ ጥናት የውል ማደስ ሂደትን ፍትሃዊ፣ ሳይንሳዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመምራት ያለመ ነው።


ያለአግባብና በየጊዜው የሚጨምር የቤት ኪራይ ዋጋ የዜጎችን የመክፈል አቅም በማዳከም ለዋጋ ንረት መባባስ አንድ ምክንያት በመሆኑ ጥናቱ በመዲናዋ ሁለንተናዊ እሴቶች ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ተብራርቷል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

ጥናቱ አከራዩ ከንብረቱ የወቅቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ ፍትሃዊ ገቢ እንዲያገኝ የሚያረጋግጥ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ተከራዩ ከገቢው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል የተረጋጋ የኢኮኖሚ ህይወት እንዲመራ ያደርጋል።


ይህ የቤት ኪራይ ገበያውን ጤናማና ሊተነበይ የሚችል በማድረግ የከተማዋን የንግድና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንደሚያረጋጋ እና ቤተሰቦች በተደጋጋሚ ቤት ከመቀየር ስጋት እንደሚታደጋቸው ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ግልጽና ህጋዊ አሰራርን በመዘርጋት በአከራይና ተከራይ መካከል የነበረውን ያለመተማመን መንፈስ ከመቅረፍ ባለፈ የደላሎችና የህገ-ወጥ ደላሎችን ጣልቃ ገብነት እንደሚያስቀር አመልክተዋል።


ዛሬ የቀረበው የዋጋ ትመና ጥናት በዘፈቀደ የተሰራ ሳይሆን የከተማዋን ነዋሪ የመክፈል አቅም መሰረት ያደረገ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች ተሳትፈዋል።

የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና በዘርፉ የሚታዩ አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በተጀመረው የዲጂታል ምዝገባ ሂደት እስካሁን ወደ አምስት መቶ ሺህ የሚጠጉ ቤቶች ወደ ሲስተሙ መግባታቸውን ቢሮው ቀደም ብሎ ማስታወቁ ይታወሳል።

በዚህም መንግሥት በየዓመቱ አንድ ጊዜ የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የገበያ ጥናት ካካሄደ በኋላ የገበያ ዕድገት መኖሩ ሲረጋገጥ በየዓመቱ ሰኔ 30 ላይ በሚያወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት የዋጋ ጭማሪውን በፐርሰንት (በመቶኛ) ይወስናል።


በተጨማሪም አብዛኞቹ ውሎች ጊዜያቸው የሚያበቃው ከሰኔ 30 በኋላ በመሆኑ በውል ስምምነት ውስጥ እያሉ ዋጋ መጨመር ፈጽሞ እንደማይፈቀድም በወቅቱ አጽንኦት ተሰጥቶ ነበር።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

23 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።