Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

ዜጎች በውሸት የፍቅር ግንኙነት እና የስጦታ ወጥመድ እስከ 500 ሺህ ብር እያጡ መሆኑ ተገለጸ

BS Bethelhem Solomon Jul 21, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 175 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ዜጎች በውሸት የፍቅር ግንኙነት እና የስጦታ ወጥመድ እስከ 500 ሺህ ብር እያጡ መሆኑ ተገለጸ

ማንኛውም ሰው ከማያውቀው እና በአካል ከማይተዋወቀው አካል እንዲህ ዓይነት የፍቅርና የስጦታ ጥያቄ ሲቀርብለት “ካለው ሰው ሁሉ እኔ ለምን ተመረጥኩ?” በማለት መጠራጠር ይገባዋል ተብሏል።


በማህበራዊ
ትስስር ገጾች ላይ በዘመናዊ መልኩ የተደራጁ እና ስሜትን መሰረት ያደረጉ የኦንላይን ማጭበርበር ወንጀሎች ሀገሪቱን እያሳሰቡ መምጣታቸውየፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።



በርካታ ዜጎች ውጭ ሀገር ነው የምኖረው የፍቅር ጓደኛ አጥብቄ እፈልጋለሁ እንዲሁም ለሞት የሚዳርግ ከባድ በሽታ ይዞኛል፤ ነገር ግን ያለኝን እጅግ ብዙ ሀብት የሚያስተዳድርልኝ እና የሚወርስልኝ ታማኝ ሰው መምረጥ እፈልጋለሁ በሚሉ የውሸት ሰበቦች እየተታለሉ ከፍተኛ ገንዘብ እየተዘረፉ ይገኛሉ።

አጭበርባሪዎቹ ሕገወጥ ድርጊታቸውን ለመፈጸም እንደ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ቴሌግራም ያሉ ታዋቂ የማህበራዊ መገናኛ መድረኮችን በስፋት ይጠቀማሉ ተብሏል



አታላዮቹ መጀመሪያ ላይ ሰዎችን በጓደኝነት ጥያቄ በመቅረብ፤ ከሚታዩት እና ከሚገኙት ሰዎች ሁሉ አንተን/አንቺን ብቻ መርጫለሁ በሚል ማራኪና አሳሳች ቋንቋ የዒላማቸውን ስሜት ይቆጣጠራሉ።



በዚህም ሳቢያ ብዙዎች እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘባቸውንና ንብረታቸውን ለቀማኞች አሳልፈው እየሰጡ መሆናቸውን የዐቃቤ ሕግ መረጃ ያረጋግጣል።


የማጭበርበሩ
መረብ እጅግ የጠነከረ እና በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን የተጠቆመ ሲሆን የወንጀሉ አፈጻጸም ሂደትም አስገራሚ መሆኑም ተነግሯል።



የመጀመሪያው አታላይ ከፍቅር ግንኙነትና ከሀብት ውርሰና ቃል ኪዳን በኋላ ራሱን ከሰወረ በኋላ፤ ሌላኛዋ ወይም ሌላኛው ተባባሪ በሌላ ስልክ ቁጥር እና በልዩ ስም በመደወል ተጎጂውን ያነጋግራሉ።



በመቀጠልም ውድ የሆነና ዶላር እንዲሁም ወርቅ የያዘ ትልቅ ዕቃ ከውጭ ሀገር ተልኮልህ/ልሻል ጉምሩክ ደርሷል፤ ነገር ግን ዕቃውን ለመረከብ የተወሰነ የጉምሩክ ክፍያ መክፈል ይጠበቅብሃል/ሻል በሚሉ አሳማኝ ንግግሮች አጭበርባሪዎቹ የተጎጂውን እምነት ለማግኘት የላኪና የተቀባይ ስም ያለበት የታሸገ ትልቅ የዕቃ ፎቶ በቴሌግራም ወይም በዋትስአፕ ይልካሉ።



ተጎጂውም በስጦታው ተማርኮ እና ዕቃው በእርግጥም መጥቷል ብሎ በማመን በተደጋጋሚ ገንዘብ በመላክ እስከ 500 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ እንዲያጣ ይደረጋል።


Advertisement
Your ad could be here — contact us

የግንኙነት ሂደቱ አብዛኛውን ጊዜ በፌስቡክ ተጀምሮ ወደ ግል መልዕክት ማቀበያ መድረኮች እንደ ዋትስአፕ እና ቴሌግራም እንደሚሸጋገር የተጠቆመም ሲሆን ህብረተሰቡ መሰል ወንጀሎች ሰለባ እንዳይሆን ጥልቅ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።



 ማንኛውም ሰው ከማያውቀው እና በአካል ከማይተዋወቀው አካል እንዲህ ዓይነት የፍቅርና የስጦታ ጥያቄ ሲቀርብለት ካለው ሰው ሁሉ እኔ ለምን ተመረጥኩ? በማለት መጠራጠር ይገባዋል ተብሏል።



በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብቻ 100 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ መጠን ያላቸው 80 በላይ ዋና ዋና የክስ መዝገቦች በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አማካኝነት በንጹሐን ዜጎች ላይ በተፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች ዙሪያ መመስረታቸው ታውቋል።

በየክፍለ ከተማው እና በሌሎች የታችኛው የስልጣን እርከኖች ላይ የተመሰረቱትን ሌሎች ተመሳሳይ የክስ መዝገቦች ሲታከሉበት ደግሞ፤ ችግሩ የደረሰበትን አጠቃላይ አሳሳቢ መጠን እና የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ከፍ ያለ መሆኑን እንደሚያሳይ ተመላክቷል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

52 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።