Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ቢዝነስ

ኢትዮጵያ 157 ሚሊዮን የሞባይል ገንዘብ አካውንቶች ቢኖሯትም ከ15 በመቶ ያነሱት ብቻ አክቲቭ ናቸው ተባለ

BS Bethelhem Solomon Aug 17, 2026 1 ደቂቃ ንባብ 21 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ኢትዮጵያ 157 ሚሊዮን የሞባይል ገንዘብ አካውንቶች ቢኖሯትም ከ15 በመቶ ያነሱት ብቻ አክቲቭ ናቸው ተባለ

በአጠቃላይ የንቁ ተጠቃሚዎች መጠን ከ15 በመቶ በታች መሆኑ በሂሳብ ምዝገባ እና በእውነተኛው አጠቃቀም መካከል ሰፊ ክፍተመኖሩን ያሳያል ተብሏል


በኢትዮጵያ
157 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ገንዘብ አካውንቶች ቢመዝገቡም ንቁ አገልግሎት ላይ የዋሉት ግን 15 በመቶ እንደማያልፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

የብሔራዊ ባንክ የባንክ እና የክፍያ ስርዓቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ዳምጤ እነዚህን አኃዞች ይፋ ያደረጉት በአዲስ አበባ በተካሄደው 29ኛው "የተገናኘ ባንክ ስብሰባ እና የፈጠራ ውጤቶች እና የዕውቅና ሽልማት 2026" መድረክ ላይ እለት ባደረጉት ንግግር ነው።

አቶ ሰሎሞን እንዳብራሩት የንቁ ተጠቃሚነት መጠኑ በዲጂታል ፋይናንስ ቻናሎች መካከል የተለያየ ሲሆን ሞባይል ባንኪንግ አንጻራዊ የተሻለ አጠቃቀም ሲኖረው የሞባይል ገንዘብ እና በወኪሎች የሚደረጉ መለያዎች ግን ዝቅተኛ የንቁ ተጠቃሚነት መጠን አላቸው።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

በአጠቃላይ ሲታይ የንቁ ተጠቃሚዎች መጠን 15 በመቶ በታች መሆኑ በሂሳብ ምዝገባ እና በእውነተኛው አጠቃቀም መካከል ሰፊ ክፍተት መኖሩን ያሳያል።

በተጨማሪም በፋይናንስ አገልግሎቶች ተደራሽነት ረገድ በተለይም በከተማ እና በገጠር አካባቢዎች መካከል ያለው ልዩነት መቀጠሉን የጠቆሙት አቶ ሰሎሞን  በገጠር የሚገኙ ሰዎች መሰረታዊ የባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት አሁንም በአማካይ እስከ ስድስት ሰዓት የሚደርስ መንገድ መጓዝ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል

ብሔራዊ ባንክ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ "ሁለተኛው ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያዎች  እየተገበረ የሚገኝ ሲሆን የመጀመሪያው ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያዎች ስትራቴጂ የዲጂታል ፋይናንስ ስነ-ምህዳርን ለመዘርጋት፣ ባንክ ነክ ያልሆኑ የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢዎችን ለማስተዋወቅ እና የቴክኖሎጂ ትስስር መሠረተ ልማት ለመገንባት ትልቅ እገዛ ማድረጉን አቶ ሰሎሞን ገልጸዋል።


ኢትዮጵያ አሁን 35 በላይ ባንክ ነክ ያልሆኑ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢዎች እንዳሏት የገለጹም ሲሆን የዲጂታል ግብይት መጠኖችም ከፍተኛ እድገት አሳይተዋል ብለዋል


አቶ ሰሎሞን እንዳሉት በመላው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስነ-ምህዳር የተደረጉ ግብይቶች አሁን ባለው የበጀት ዓመት 33 ትርሊዮን ብር ደርሰዋል፤ ይህም እኤአ 2023 አጋማሽ ከነበረበት 4.7 ትርሊዮን ብር እና 2020 ከነበረበት 240 ቢሊዮን ብር ጋር ሲወዳደር እጅግ ግዙፍ ዝላይ አሳይቷል።

የብሔራዊ ባንክ ስትራቴጂ እስከ 2030 ድረስ የዲጂታል የህዝብ መሠረተ ልማት ማዕቀፍ መዘርጋትን የሚያካትት ሲሆን፤ ይህም የእውነተኛ ጊዜ የክፍያ መሠረተ ልማት፣ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እንዲሁም የውሂብ ልውውጥ ንጣፍን ያጠቃልላል።

ስትራቴጂው በተጨማሪም ክፍት የሶፍትዌር መገናኛዎች፣የደመና መድረኮች የጋራ ማጭበርበር ማካካሻ ፈንድ፣ እንዲሁም የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ፣ ቨርቹዋል ንብረቶች፣ ስቴብል ኮይኖች እና ቶኬናይዜሽን ዕቅዶችን ያካተተ ነው።

በመሆኑም የብሔራዊ ባንክ ቀጣይ ትኩረት የዲጂታል መለያዎችን ቁጥር ከማስፋፋት ወደ እውነተኛው አጠቃቀማቸው ማሳደግ እንዲሁም በተለይም በቂ አገልግሎት ባላገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ የዲጂታል ፋይናንስ ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተመላክቷል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

68 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።