Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ቢዝነስ

እውነተኛ ባለቤቶቻቸውን የማያሳውቁ ኩባንያዎችን እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ደንብ ወጣ

BS Bethelhem Solomon Aug 25, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 760 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
እውነተኛ ባለቤቶቻቸውን የማያሳውቁ ኩባንያዎችን እስከ 500 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ደንብ ወጣ

ይህ አዲስ ደንብ ባለሥልጣናት የገንዘብን ህገወጥ ዝውውር እና ሽብርተኝነት ፋይናንስ አቅርቦትን ለመከላከል በሚያደርጉት ጥረት እና ማዕከላዊ የሆነ የእውነተኛ ባለቤቶች መዝገብ ለማቋቋም በሚያዘጋጁት ዝግጅት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል።



በኢትዮጵያ
ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች እና ሌሎች ሕጋዊ አካላት ድርጅቶቹን በባለቤትነት የሚቆጣጠሩትን ወይም የመጨረሻዎቹን እውነተኛ ባለቤቶች እስከ መጪው ጥር ወር ድረስ እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ አዲስ ጥብቅ ደንብ ወጣ።


ደንቡንለማክበር እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ የንግድ ፈቃድ እገዳ እና ከመንግሥት የግዥ ጨረታዎች ሙሉ በሙሉ መታገድን የመሳሰሉ ጠንካራ እርምጃዎችን እንደሚያስከትል ተገልጿል።

ሐምሌ 3 ቀን 2018 . በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ የወጣው "የሕጋዊ አካላት እውነተኛ ባለቤትነት መረጃ ግልጽነት ደንብ" ሕጋዊ አካላት ባለቤቶቻቸውን በመለየት መረጃውን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲይዙ የሶስት ወራት ማለትም እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2019 . ለንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ ደግሞ የስድስት ወራት እስከ ጥር 2 ቀን 2019 . ጊዜ ሰጥቷል።


ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው የሽግግር ጊዜውን እስከ ሁለት ወራት ማራዘም እንደሚችል በደንቡ ተቀምጧል።

ይህ አዲስ ደንብ ባለሥልጣናት የገንዘብን ህገወጥ ዝውውር እና ሽብርተኝነት ፋይናንስ አቅርቦትን ለመከላከል በሚያደርጉት ጥረት እና ማዕከላዊ የሆነ የእውነተኛ ባለቤቶች መዝገብ ለማቋቋም በሚያዘጋጁት ዝግጅት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

በአዲሱ ደንብ መሠረት እንደ አክሲዮን ማኅበራት ያሉ ድርጅቶች 10 በመቶ እና ከዚያ በላይ ድርሻ ያላቸው ግለሰቦች እንደ እውነተኛ ባለቤት የሚቆጠሩ ሲሆን፤ ሕጉ ከድርጅቶች ጀርባ ባሉ ስማቸው ብቻ የሚታዩ ግለሰቦች ወይም የተወሳሰቡ የኮርፖሬት መዋቅሮች ራሳቸውን መደበቅ እንዳይችሉ የሚያደርግ ነው።


ይሁን እንጂ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት ስር ያሉ የፌዴራል ወይም የክልል ኢንተርፕራይዞች፣ ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ የመንግሥት፣ የሃይማኖት እና የፖለቲካ ተቋማት ከዚህ ደንብ ነፃ ተደርገዋል።

ደንቡን የሚተላለፉ ድርጅቶች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች ከባድ ቅጣቶችን ያካተቱ ሲሆን መረጃውን ዘግይቶ ማቅረብ፣ ያልተሟላ ወይም የተሳሳተ መረጃ መስጠት እንዲሁም መረጃውን 14 ቀናት ውስጥ አለማሻሻል 100,000 እስከ 500,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ያስከትላል።


ከዚህም ባለፈ መደበኛ የባለቤትነት ግምገማዎችን አለማድረግ ወይም ኃላፊነት ያለው መረጃ-ምዝገባ ኦፊሰር አለመሾም የንግድ ፈቃድ እገዳን ወይም ስረዛን እንደሚያስከትል ተመላክቷል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በህግ አከባበር ላይ ችግር ያለባቸውን ተቋማት ስም በድረ-ገጹ ላይ ሊያትም የሚችል ሲሆን የፌዴራል የይፋዊ ግዥ አገልግሎትም ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር መረጃዎችን በቀጥታ እንደሚያገኝ ተገልጿል። እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፍቃድ የሰጧቸውን ተቋማት መረጃ እንዲጠይቁ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።

የብሔራዊ ፀረ-ገንዘብ ህገወጥ ዝውውር ኮሚቴ የመረጃ ቋቱን ማዕከላዊ የማድረግ ሥራዎችን እያፋጠነ የሚገኝ ሲሆን ሙሉ የማስፈጸሚያ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት እስከ መጋቢት 2017 . ድረስ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል።


ለሺዎች ለሚቆጠሩ በግል ባለቤትነት ለተያዙ ኩባንያዎች ግን አሁን ላይ ያለው ዋነኛ ግዴታ የድርጅቶቻቸውን እውነተኛ ባለቤቶች በመለየት ሰንደዶችን በማዘጋጀት እና ከታቀደው የጊዜ ገደብ በፊት መረጃውን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ መሆኑ ታውቋል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

80 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።