Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

“እነሱን ፈቃድ ለመጠየቅ እንሄዳለን ያለው ማን ነው?” ለግብፅ የተሰጠ ምላሽ

BS Bethelhem Solomon Aug 21, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 343 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
“እነሱን ፈቃድ ለመጠየቅ እንሄዳለን ያለው ማን ነው?” ለግብፅ  የተሰጠ ምላሽ

ግብፅ ለኢትዮጵያ የውሃ ልማት ፈቃድ መስጠት አለባት መባሉ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነው ተባለ


ኢትዮጵያ
ታላቁን የህዳሴ ግድብ የማንንም ፈቃድ ሳያስፈልጋት እንደገነባችው ሁሉ በሌሎች ወንዞች ላይም ተመሳሳዩን ተግባር ማከናወን እንደምትችል የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር  በይፋ አስታወቀ።


የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ / ሃብታሙ ኢተፋ ከመንግስታዊው «ፐልስ ኦፍ አፍሪካ» ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ ራሷን የቻለች ሉዓላዊ ሀገር እንደመሆኗ የውሃ ሀብቷንም ሆነ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶቿን አልምታ ለመጠቀም የየትኛውንም አካል ፈቃድ መጠየቅ እንደማያስፈልጋት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።


ሚኒስትሩ አክለውም ሀገሪቱ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የውስጥ ሀብቷን በራሷ አቅም የማልማት ሙሉ መብት እንዳላት አስምረውበታል።

 

ይህ መግለጫ የተሰጠው ሰሞኑን የግብፅ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ተጨማሪ ሦስት ግድቦችን ልትገነባ ነው በሚል ባሰሙት ተቃውሞ እና ሀገራቸው ይህንን እንዲሆን እንደማትፈቅድ በገለጹበት ወቅት ነው።


በዚህም ግብፅ ኢትዮጵያ ወደ አሳሪ ስምምነት መምጣት እንዳለባት እና ተጨማሪ ግድቦችን ለመገንባትም ሆነ የዓባይን ውኃ ለመጠቀም የግብፅ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ አጥብቃ መከራከሯ ይታወሳል።


ሚኒስትሩ የግብፅን አቋም ፍጹም ውድቅ በማድረግ ራሳችንን የቻልን ሀገር ነን፤ ሕዝብ አለን፣ መሬት አለን፣ መንግሥት አለን፣ ፖሊሲ አለን፤ ይህንንም አይረዱትም ብለዋል።


አክለውም ይህንንም ባለመረዳታቸው ወደ ቅኝ ግዛት አስተሳሰብ እንደሚሄዱ እና ለዘመናት ሲቃወሙት የቆዩትን አካሄድ እንደሚያንጸባርቁ በመጥቀስ እነሱን ፈቃድ ለመጠየቅ እንሄዳለን ያለው ማን ነው? ሲሉ ጥያቄ አዘል ምላሽ ሰጥተዋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

/ ሃብታሙ አያይዘውም የሕዳሴው ግድብ ዋና ዓላማ በሌሎች ሀገራት ላይ ጉዳት ማድረስ ሳይሆን የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ለቀጣናው ሀገራት ሁሉ የሚተርፍ መሆኑን ጠቁመዋል።


አሁን
ላይ ሀገሪቱ ለጎረቤት ሀገራት ጅቡቲ፣ ለኬንያ እና ለሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ሚኒስትሩ ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን በኩልም ተጨማሪ የኃይል ፍላጎቶች እየቀረቡ መሆናቸውን አንስተዋል።


በተጨማሪም ሚኒስትሩ በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል እውነተኛ ትብብርና ቅንጅት እንዲኖር ጥሪ ያቀረቡ ቢሆንም የግድቡን የጋራ አስተዳደር ጥያቄ ግን በቁጣ ውድቅ አድርገውታል። የውሃ ሀብትን ማልማት ፍጹም የሀገር የውስጥ ጉዳይ መሆኑንም አስምረውበታል።

 

በሌላ በኩል ግብጽ የዓባይን ውሃ በስፋት በመጠቀም በርካታ በረሃዎችን በማልማት ከተሞችን እንዲሁም አዳዲስ የልማት ቦታዎችን እየፈጠረች ትገኛለች።


በዚህ
ዓመትም በርካታ ዜጎቿን የወንዙን ውሃ ተጠቅማ በአዲስ ስፍራዎች እንደምታሰፍር ወቅታዊ መረጃዎች ያሳያሉ።
ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ እነዚህን የውጭ ተፅዕኖዎች እና ተቃውሞዎች በመሰረዝ ኢትዮጵያ የልማት ስራዎቿን ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

80 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።