Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ ለነበሩ አካላት አዲስ የግብር ስሌት አሰራር ተዘረጋ

BS Bethelhem Solomon Oct 12, 2026 1 ደቂቃ ንባብ 13 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ ለነበሩ አካላት አዲስ የግብር ስሌት አሰራር ተዘረጋ

አዲሱ አሰራር በሙያዊ አገልግሎቶች ዘርፍ የሚስተዋለውን የግብር ስወራ ለመቀነስ ህጋዊ አሰራርን ለማስፈን እና ህግ አክባሪነትን ለማጠናከር አልሞ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።


የአዲስ
አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ አካላት የሚሆን አዲስ የግብር ስሌት አሰራር መዘረጋቱን አስታወቀ።



አዲሱ አሰራር ጠበቆችን፣ የኢንሹራንስ ወኪሎችን፣ የኢንሹራንስ ጉዳት ገማቾችን እና ተመሳሳይ የሙያ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አካላትን የሚያጠቃልል ሲሆን የሂሳብ መዝገብ ሳያቀርቡ ሲቀሩ ይፈጸም የነበረውን የረጅም ጊዜ ህጋዊ እና አሰራራዊ ክፍተት ለመሙላት ያለመ ነው።

 

እንደ ቢሮው ማብራሪያ እነዚህ አካላት ህጋዊ የሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ግዴታ ቢኖርባቸውም አብዛኞቹ መዝገብ ሳያቀርቡ ሲቀሩ የነበረውን አሰራር ለመቀየር አዲሱ መመሪያ ግልጽ የስሌት ማዕቀፍ አስቀምጧል።


በዚህም መሰረት ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ባላቀረቡበት ሁኔታ ከአጠቃላይ ገቢያቸው ላይ 35 በመቶው እንደ ወጪ ታስቦ የሚቆረጥ ሲሆን ቀሪው 65 በመቶ ደግሞ ግብር የሚከፈልበት ገቢ እንደሆነ ተቆጥሮ ግብራቸው እንዲሰበሰብ ይደረጋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

አዲሱ አሰራር በሙያዊ አገልግሎቶች ዘርፍ የሚስተዋለውን የግብር ስወራ ለመቀነስ ህጋዊ አሰራርን ለማስፈን እና ህግ አክባሪነትን ለማጠናከር አልሞ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።


ይህ የግብር ስሌት አሰራር ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ ጊዜያዊ ማዕቀፍ ሲሆን ከዚህ የግብር ዘመን በኋላ ባለሙያዎቹ ህጋዊ የሂሳብ መዝገብ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ የማስተካከያ እርምጃዎችና የቃል መሐላ ስነ-ስርዓቶች እንደሚከናወኑ ቢሮው ገልጻል።


አዲሱ መመሪያ በሚጠይቀው መሰረት በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ስራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል እና አገልግሎት ለመስጠት የሂሳብ መዝገብ አያያዝ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

 

ይህ እርምጃ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግብር መሰረቱን ለማስፋት እና የገቢ ስብሰባውን ለማሳደግ እያደረገ ያለው ሰፊ የፖሊሲ ጥረት አካል እንደሆነ ተመላክቷል።
በቅርብ ዓመታት ከተማዋ የግብር ተመንን ሳትጨምር በታክስ አስተዳደር፣ በኦዲት ስርዓት ማሻሻያ እና በስብሰባ ስልቶች ላይ ባደረገችው ኢንቨስትመንት ከፍተኛ የገቢ እድገት ማስመዝገብ ችላለች።

 

በሙያዊ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ በርካታ ባለሙያዎች በተናጠል የሚሰሩ መደበኛ የንግድ መዋቅር የሌላቸው እና ክፍያዎችን በጥሬ ገንዘብ የሚቀበሉ በመሆናቸው ገቢያቸውን በትክክል ለመከታተል አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቷል።



ይህም በዘርፉ ስፋት ላለው ያልተረጋገጠ የግብር ግምት፣ ገቢን አነስተኛ አድርጎ ለማሳወቅ እና ህጋዊ የሂሳብ መዝገብ ያለማቅረብ ፈተና መንስኤ ሆኖ የቆየ ሲሆን አዲሱ መመሪያ እነዚህን ተደጋጋሚ እና ዘላቂ ችግሮች በመቅረፍ ባለሙያዎች ወደፊት ህጋዊ የሂሳብ መዝገብ በመያዝ ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚያስገድድ ይሆናል።

 

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

89 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።