Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ለሁሉም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ እንዲያሟሉ ሊገደዱ ነው

BS Bethelhem Solomon Jun 17, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 12 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ለሁሉም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ እንዲያሟሉ ሊገደዱ ነው

አዲሱ መመሪያ የሚገጠሙት ቀበቶዎች ዓለም አቀፍ የደህንነት መስፈርቶችን ያሟሉ እንዲሆኑ ያስገድዳል።


በኢትዮጵያ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ውስጥ ከፊት መቀመጫ እስከ ኋላ ወንበር ለሚቀመጡ ተሳፋሪዎች በሙሉ ደረጃውን የጠበቀ የደህንነት ቀበቶ እንዲገጠም የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።


የኢትዮጵያ መንገድ ደህንነትና መድኅን ፈንድ አገልግሎት እንደገለጸው በአገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የትራፊክ አደጋ የመቀነስ ጥረት አካል የሆነው ይህ መመሪያ ተሽከርካሪዎች ለተሳፋሪዎች ደህንነት ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው።

በአገልግሎቱ የመንገድ ደህንነት ህግ ትግበራ ዴስክ ሃላፊ / ብርክት ባህሩ እንደገለጹት አዲሱ መመሪያ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ውስጥ የደህንነት ቀበቶ ግዴታ ከአሽከርካሪው አልፎ ከፊት መቀመጫ እስከ ኋላ ወንበር ድረስ ለሚቀመጡ ተሳፋሪዎች በሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስገድዳል።



በአሁኑ
ወቅት በብዙ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገኙ ቀበቶዎች አደጋን የመከላከል አቅም እንደሌላቸውና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መሆናቸው በችግርነት የተለየ ሲሆን አዲሱ መመሪያ የሚገጠሙት ቀበቶዎች ዓለም አቀፍ የደህንነት መስፈርቶችን ያሟሉ እንዲሆኑ ያስገድዳል።


Advertisement
Your ad could be here — contact us

በዚህም ከውጭ ለሚገቡም ሆነ በሃገር ውስጥ ለሚገጣጠሙ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ደረጃውን የጠበቀ የደህንነት ቀበቶ መግጠም ግዴታ የሚያደርግ ሲሆን ቀደም ሲል አገልግሎት ላይ ያሉ የቆዩ ተሽከርካሪዎችም በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ደረጃውን የጠበቀ የደህንነት ቀበቶ እንዲያስገጥሙ ይደረጋል።


በተጨማሪም አዲሱ መመሪያ በአሁኑ ወቅት ለፍትህ ሚኒስቴር የተላከ ሲሆን ህጉ ሲጸድቅ በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገባ ታውቋል።



አገልግሎቱ ህጉን ወደ ተግባር ከመቀየሩ በፊት ስለ ደህንነት ቀበቶ አጠቃቀም ጥቅምና አስፈላጊነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጿል።


ይህ መመሪያ ተፈጻሚ ሲሆን በተለይም በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች ጊዜ በሰው ህይወትና አካል ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።


ከዚህ ቀደም የነበረው አሠራር "የተሸከርካሪ የደህንነት ቀበቶ በተሸከርካሪ ወንበሮች ላይ እንዲኖር እና ተግባራዊ እንዲደረግ ወጣው  መመሪያ ቁጥር 44/2013" ይተዳደር ነበር።


ይህ
የቀድሞ መመሪያ በተለይም በአሽከርካሪዎች ላይ የደህንነት ቀበቶ እንዲኖር በማስቻል አደጋዎችን ለመቀነስ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ህጉን ባልተገበሩት  ላይም ህጋዊ እርምጃ ሲወሰድ ቆይቷል።


ሆኖም በርካታ ተሽከርካሪዎች ቀበቶ ቢኖራቸውም ቀበቶዎቹ በትክክል ከአደጋ የማይከላከሉና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መሆናቸው በችግርነት በመለየቱ በመዘጋጀት ላይ ያለው አዲሱ መመሪያ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከፊት መቀመጫ አንስቶ እስከ ኋላ ወንበር ለሚቀመጡ ተሳፋሪዎች በሙሉ የደህንነት ቀበቶ እንዲገጥሙ የሚያስገድድ ሁኗል።


በተጨማሪም
አዲሱ መመሪያ የደህንነት ቀበቶ ግዴታን ከፊት እስከ ኋላ መቀመጫዎች በማስፋትና የደረጃ ጥራትን በማረጋገጥ የመንገድ ደህንነትን ለማስጠበቅ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።


BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

9 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።