Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

የበሬ ስጋ ቅርጫ ዋጋ ከ18,000 እስከ 30,000 ብር መድረሱ ተሰማ

BS Bethelhem Solomon Sep 8, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 504 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የበሬ ስጋ ቅርጫ ዋጋ ከ18,000 እስከ 30,000 ብር መድረሱ ተሰማ

የዘርፉ ባለሙያዎች ይህ የዋጋ ግሽበት በቀጥታ ከክልል የከብት ገበያዎች የሚነሳ እና የምግብ ዋጋ መጨመርን እንዲሁም የተሻሻሉ የመጓጓዣ ሎጂስቲክስ ወጪዎችን የሚያንጸባርቅ መሆኑን አስረድተዋል።



በዲጂታል
መድረኮች እና በኦንላይን የሚከናወነው የበዓል የበሬ ርጫ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቦ ከዚህ ቀደም በአማካይ 10,000 ብር ይሸጥ የነበረ አንድ መደብ ድርሻ አሁን ላይ እስከ 30,000 ብር መድረሱ ተመላክቷል።




ዲጂታል አሠራሮች በመጀመሪያ ሲጀመሩ አንድ መደብ የቅርጫ ድርሻ በአማካይ 10,000 ብር ገደማ ይሸጥ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ የዋጋው ማሻቀብ ተባብሶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ታውቋል።



በዚህም በሁኔታዎች መለዋወጥ ምክንያት ለደለቡ  በሬዎች የወጣው ዋጋ ጨምሮ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የበዓል መደብ ድርሻዎች 18,000 እስከ 30,000 ብር ደርሰዋል።




የዘርፉ ባለሙያዎች ይህ የዋጋ ግሽበት በቀጥታ ከክልል የከብት ገበያዎች የሚነሳ እና የምግብ ዋጋ መጨመርን እንዲሁም የተሻሻሉ የመጓጓዣ ሎጂስቲክስ ወጪዎችን የሚያንጸባርቅ መሆኑን አስረድተዋል።

 

በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ከተሞች የሚከበረው የዘንድሮው አዲስ ዓመት ከከብቶች ዕርድ እስከ ዕለታዊ ንግድ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እየታገዘ ቢሆንም ከባድ የዋጋ ግሽበት እና የባህል መሸርሸር ስጋቶች አብረውት ማሻቀባቸው ተገልጿል።



ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በቴሌግራም ቻናሎች፣ በፌስቡክ ግሩፖች እና በሞባይል መተግበሪያዎች እየተከናወነ ያለው የቅርጫ ሥርዓት በሰፊው ሕዝብ ዘንድ ትኩረት የሳበ ቢሆንም የዘንድሮው በዓል የገበያ እና የፋይናንስ ሚዛን እንዲሁም የዋጋ ጭማሪ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

እየጨመረ የመጣው ይህ የዲጅታል ቅርጫ ተወዳጅነት ቢኖረውም የዘንድሮው የዲጂታል ቅርጫ ገበያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች እንደገጠሙት ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል።



በዚህም የደንበኞች ፍላጎት ባለፉት ዓመታት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ቀንሷል የተባለ ሲሆን ይህም በዋናነት በከብት ዋጋ ላይ ባለው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና ከአዲስ ዓመት ጋር በሚመጡ የግል ትምህርት ቤት የምዝገባ ክፍያዎች እና የደንብ ልብስ ግዢዎች  ምክንያት የተከሰተ ነው ተብሏል

 

ዲጂታል ቅርጫው ሥራ ለሚበዛባቸው የከተማ ባለሙያዎች እንዲሁም በአፓርታማና በኮንዶሚኒየም ኑሮ ውስጥ ያለውን የጊዜ ጥበት የሚፈታ  ድልድይ  መሆኑ የሚታወቅ ነው።



ባህላዊ ዕርድ የሚከናወንባቸው አደባባዮች ባለመኖራቸው፣ እንዲሁም የረጅም ሰዓታት ሥራ እና የትራፊክ ማነቆ ባለባት አዲስ አበባ ቅርጫው ደጃፍ ላይ መድረሱ ትልቅ እፎይታ ቢሆንም ይህ አዝማሚያ የኢትዮጵያን የበ አከባበር እና ማኅበራዊ ንኙነት በቀስታ የሚሸረሽር  ነው የሚል ክርክር ማስነሳቱ አልቀረም።



ይሁን እንጂ እነዚህ የቅርጫ ድርጅቶች ከዲጂታል አቅማቸው በተጨማሪ  ባህላዊ ተቆጣጣሪዎችን እና አዛውንቶችን በመያዝ  ሂደቱን እንደሚያስተባብሩ የሚገልጹ ሲሆን ደንበኞችም ወደ ማዕከላቸው በመሄድ ሂደቱን እንዲመለከቱ እድል እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።



BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

80 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።