Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

የሶላር ኃይል ተጠቃሚ አካባቢ ነዋሪዎች ያለምንም ክፍያ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እንዲያስገቡ ተወሰነ

BS Bethelhem Solomon Jun 20, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 135 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የሶላር ኃይል ተጠቃሚ አካባቢ ነዋሪዎች ያለምንም ክፍያ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እንዲያስገቡ ተወሰነ

ይህንን የነፃ ቆጣሪ አቅርቦት የሶላር የኃይል አቅርቦት በተገነባባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተገልጿል።


የኢትዮጵያ
ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ ግሪድ መስመር ርቀው በሚገኙ የገጠር ከተሞች የኢነርጂ ተደራሽነትን ለማስፋት በሚያደርገው ጥረት በሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በተሸፈኑ አካባቢዎች ለሚኖሩ አዲስ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች የኤሌክትሪክ ቆጣሪን ያለምንም ክፍያ በነፃ እንዲያስገቡ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

ይህ ውሳኔ በይፋ የተበሰረው በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ሆኮ ወረዳ ሆዲ ቦኩ ከተማ በዛሬው ዕለት በተመረቀው የሆዲ ቦኩ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው

ከዓለም ባንክ በተገኘ 227 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ የተገነባው የሆዲ ቦኩ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፤525 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው።


ፕሮጀክቱ ከተማዋን እና አካባቢዋን በዘላቂ የኃይል ምንጭ ለማስተሳሰር የሚያስችል ሲሆን የማህበራዊ ተቋማትን ጨምሮ 2 ሺህ በላይ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል አቅም ተገንብቶለታል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

የአገልግሎቱ የቴክኒክ ቡድን እንደገለጸው የኃይል አቅርቦቱን ተደራሽ ለማድረግ 1.2 ኪሎ ሜትር መካከለኛ እና 10.5 ኪሎ ሜትር ዝቅተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተዘርግተዋል።


ከዚህም በተጨማሪ ሶስት ትራንስፎርመሮች ተተክለው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን በአገልግሎቱ በተመቻቸ የነፃ ቆጣሪ ዕድል አማካኝነት በአሁኑ ወቅት 487 አባወራዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይህንን አዲስ አሰራር የዘረጋበት ዋና ዓላማ የዜጎችን የኢኮኖሚ አቅም ሳይገድብ እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል የኃይል ተጠቃሚ እንዲሆንና ወደ ተሻለ ዘመናዊ ሕይወት እንዲሸጋገር ለማስቻል መሆኑን ገልጿል።


አገልግሎቱ እንደገለጸው ይህ እርምጃ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ሳይገድባቸው የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ትልቅ እገዛ ያደርጋል።

በገንዘብ እጥረት ሳቢያ ከዘመናዊ አኗኗር ወደኋላ የሚቀር ማህበረሰብ እንዳይኖር ለማድረግ ያለመው ይህ የነፃ ቆጣሪ አቅርቦት የሶላር የኃይል አቅርቦት በተገነባባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተመላክቷል።

ባለፉት ዓመታት ከዋናው የኤሌክትሪክ ግሪድ ርቀው በሚገኙ የገጠር ከተሞች የፀሐይ ኃይልን የማድረስ ስራ በአጽንኦት ሲከናወን የቆየ ሲሆን በዚሁ መሰረት የሆዲ ቦኩን ማመንጫ ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ 43 የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች የተገነቡ ሲሆን 10 ሺህ በላይ አባወራዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም አገልግሎቱ የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም ችግር ለመፍታት ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ጋር ለተገናኙ ደንበኞች የቆጣሪ ክፍያን በረጅም ጊዜ የክፍያ አማራጭ እንዲያገኙ ማመቻቸቱ የሚታወስ ሲሆን የነፃ ቆጣሪ አሰራሩን ከሶላር ፕሮጀክቶች ጋር በማጣመር የገጠር ልማትን ለማፋጠን ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

14 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።