Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ቢዝነስ

ግዙፉ የነዳጅ አቅራቢ ኢኖክ ለኢትዮጵያ ነዳጅ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቀቀ

BS Bethelhem Solomon Jun 22, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 233 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ግዙፉ የነዳጅ አቅራቢ ኢኖክ ለኢትዮጵያ ነዳጅ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቀቀ

ሁለቱ ወገኖች በተለይም ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ የነዳጅ ምርቶች አቅርቦትን ለማቀላጠፍ እና በቅርቡ በጅቡቲ እየተከናወኑ ያሉ የኢነርጂ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ግዙፉ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የነዳጅ ዘይትና ጋዝ አቅራቢ ኩባንያ ኤሚሬትስ ናሽናል ኦይል ካምፓኒ (ENOC) የፔትሮሊየም ምርቶችን ለኢትዮጵያ ገበያ በስፋት ለማቅረብ የሚያስችለውን የመጨረሻ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል።

የጅቡቲ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ / ጃማ መሀመድ ሀሰን፣ የኢኖክ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የኤች...ኤል የቦርድ ሰብሳቢ ከሆኑት አቶ ሁሴን ሱልጣን ሉታ ጋር በጅቡቲ ቢሮአቸው በኤነርጂያ ፓርክ ተወያይተዋል።


የአቶ ሁሴን ሱልጣን ሉታ የጅቡቲ ጉብኝት አዲሱን የኢነርጂ ሚኒስትር ለመተዋወቅ እና የሁለቱን ወገኖች የትብብር ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የክብር ጉብኝት መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የኤች..ኤል (HTL) ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፋሃድ አብዱልራህማን አስካር፣ የኤች...ኤል (HDTL) ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኦማር ካሱ እንዲሁም ከሚኒስቴሩ እና ከጅቡቲ አለም አቀፍ የሃይድሮካርቦን ማህበር የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ወቅት የዶራሌህ ነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል ለኢትዮጵያ ገበያ እያቀረበ ያለው የነዳጅ ምርት አቅርቦት አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተነስቷል።


በዚህም ሁለቱ ወገኖች በተለይም ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ የነዳጅ ምርቶች አቅርቦትን ለማቀላጠፍ እና በቅርቡ በጅቡቲ እየተከናወኑ ያሉ የኢነርጂ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን መግባባት ላይ ደርሰዋል።


በሌላ በኩል በጅቡቲ የሚከናወኑት ስትራቴጂያዊ የኢነርጂ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ የተሰጣቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል የባቡር መስመርን ከነዳጅ ማከማቻ ጣቢያዎች ጋር የማገናኘት ስራ፣ ተጨማሪ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ገንዳዎችን የመገንባት ስራ፣ የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ  ማከማቻ ተቋማት ግንባታ እና የነባሩን የባህር መርከቦች ማረፊያ የማስፋፋት ስራዎች ይገኙበታል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

የኢኖክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሁሴን ሱልጣን ሉታ ፕሮጀክቶቹ ለሁለቱም ኩባንያዎች ለጅቡቲ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያላቸውን ከፍተኛ ፋይዳ በማብራራት አጋርነቱ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ  መሆኑን አስረድተዋል።


አቶ ሁሴን ሱልጣን ሉታ ፕሮጀክቶቹን እውን ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት በመግለጽ ከጅቡቲ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ / ጃማ መሀመድ ሀሰን በበኩላቸው የፕሮጀክቶቹን ሂደትና የጥናት ሰነዶችን እንዲቀርቡላቸው ጠይቀው መንግስታቸው የፕሮጀክቶቹን ስኬት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።


ውይይቱን በጋራ የመሩት ሁለቱ ወገኖች በፕሮጀክቶቹ ላይ ተመሳሳይ አቋም ላይ በመድረስ የያዙትን ግብ ለማሳካት በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ታውቋል።


ኤሚሬትስ ናሽናል ኦይል ካምፓኒ (ENOC) ቀመጫውን በዱባይ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያደረገ በዱባይ መንግስት ባለቤትነት ስር የሚተዳደር ግዙፍ የነዳጅ ዘይትና ጋዝ ኩባንያ ሲሆን በነዳጅ ፍለጋና ምርት፣ በማጣራት፣ በነዳጅ ማከማቻ፣ በችርቻሮ ንግድ፣ እንዲሁም በነዳጅ ማጓጓዣ ዘርፎች በሰፊው የተሰማራ ነው።


በተጨማሪም በርካታ የዓለም ሀገራት የንግድ ስራዎቹን የሚያከናውን ሲሆን ለኢነርጂ፣ ለኢንዱስትሪ እና ለተለያዩ የንግድ ተቋማት የነዳጅ እና የጋዝ ምርቶችን ያቀርባል።


BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

15 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።