Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

አዲሱ የቤት ኪራይ ውል እድሳትና የዋጋ ጣሪያ ላይ ጥብቅ ክልከላ ተጣለ

BS Bethelhem Solomon Jul 8, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 376 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
አዲሱ የቤት ኪራይ ውል እድሳትና የዋጋ ጣሪያ ላይ ጥብቅ ክልከላ ተጣለ

የዋጋ ጭማሪውና የውል እደሳቱ መነሻ የሚሆነው ከዚህ ቀደም በነበረው ውል ላይ በተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ብቻ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።


የአዲስ
አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ መደበኛ ያልሆኑ አሰራሮችን ለመግታት በማሰብ 2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ እንዲጸድቅ መወሰኑን አስታውቋል።


ይህ ውሳኔ ቀደም ሲል በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት የተወሰነ ሲሆን በከተማዋ የተካሄደ ሳይንሳዊ ጥናትንና የነዋሪውን የመክፈል አቅም ያገናዘበ መሆኑ ተገልጿል።

ይህንን ተከትሎ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 . ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች በይፋ መተግበር መጀመሩን ቢሮው አስታውቋል።



ይሁን እንጂ የዋጋ ጭማሪውና የውል እደሳቱ መነሻ የሚሆነው ከዚህ ቀደም በነበረው ውል ላይ የተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ብቻ መሆኑን ቢሮው አፅንኦት ሰጥቶ ገልጿል።


ቢሮው አዲሱን የውል እድሳት ምዝገባ እና የተቀመጠውን የዋጋ ጣሪያ ወደ ጎን በመተው የሚፈጸሙ ማናቸውም ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ጥብቅ ክልከላ ጥሏል።



በዚህም መሠረት በቢሮው ከተመዘገበው ውል እንዲሁም ከሚሰጠው አቅጣጫ ውጭ ልዩ ውል በሚል የሚፈጸሙ የመንደር ውሎች፣ ከሕጋዊ አሰራር ውጭ የሚደረጉ የአካባቢ ውሎች፣ እንዲሁም በጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) አካባቢ የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት ሕገ-ወጥ ውሎች ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው።



ማንኛውም አከራይ እና ተከራይ እነዚህን የተከለከሉ ሕገ-ወጥ ውሎች ይዘው ሲገኙ ወይም ከተቀመጠው 11.5% የዋጋ ጭማሪ ጣሪያ በላይ ፈጽመው ከተገኙ ቢሮው ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስጠንቅቋል።


Advertisement
Your ad could be here — contact us

የዋጋ ጭማሪውን እና አተገባበሩን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ የሚገኙ ሲሆን የሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አሻግሬ ዘውዱ ባለፉት ሁለት አመታት አከራይና ተከራይ በመነጋገር ግብር የሚታሰብበትን የኪራይ ገንዘብ በባንክ፣ የተቀረውን በግልጽ እየተቀበሉ እንደነበር በመጥቀስ፣ መንግስት ይህንን በአግባቡ መቆጣጠር እንዳልቻለ መግለጻቸው ይገኝበታል።


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ላፊ / ቅድስት ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው ጥናቱ የኑሮ ሁኔታን ያገናዘበና ሁለቱም ወገኖች የማይጎዱበት መሆኑን ይገልጻሉ።



ለዚህ ስራ የተመደቡ ኮሚቴዎች ያሉ በመሆኑ፤ በሚመጡ ጥቆማዎች መሰረት ችግሮችን እንደሚፈቱና አሰራሩን ለማዘመን እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።


አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ቤትን መከራየት እንዲችሉ መንግስት በራሱ ገንብቶ ቢያቀርብ፣ እንዲሁም የግል የቤት አልሚ ድርጅቶች ከሚሸጧቸው ቤቶች የተወሰኑትን እንዲያከራዩ የሚያስገድድ የህግ ማዕቀፍ ቢኖር እና የቤት አቅርቦቱ እንደልብ ካለ የተረጋጋ የኪራይ ዋጋ ሊኖር እንደሚችል ይታመናል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

53 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።