Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

ቀይ ባሕርን ያጣነው በውስጥ ስንፍናና በውጭ ጣልቃ ገብነት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ

BS Bethelhem Solomon Jul 15, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 623 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ቀይ ባሕርን ያጣነው በውስጥ ስንፍናና በውጭ ጣልቃ ገብነት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን መሻትና ጥቅም ማስቆም የሚችል ኃይል እንደሌለ አጽንኦት ሰጥተዋል።


ቀይ
ባሕርን ያጣነው እኛ ስንጨቃጨቅ ጊዜ ጠብቀው ጣልቃ በመግባት መሻታችንን እንዳንከውን ባደረጉ ኃይሎች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ልጸዋል


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተጀመረው ታሪካዊ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

በንግግራቸው ወቅት ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ ሆና የጂኦግራፊ እስረኛ የሆነችበት ዋና ምክንያት ያልተመረጠ እና ያልተወያየ መንግሥት በፖለቲካ ሸፍጥ፣ ሴራ እንዲሁም በውስጥ መከፋፈልና ስንፍና ውስጥ መውደቁ እንደሆነ አብራርተዋል።


ይህ ክስተት እንደ አንድ እኩይ እሳቤ መገለጫ የሚወሰድ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን መሻትና ጥቅም ማስቆም የሚችል ኃይል እንደሌለ አጽንኦት ሰጥተዋል።


አያይዘውም "ያልተሳካልን በውስጥ ስንፍናችን እንጂ አቅም አጥተን አይደለም" ሲሉ አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መድረኩን "አንዳንድ አጋጣሚዎች ያሻችሁን እንድትጽፉ ብዕርና ብራና ያቀብሏችኋል" በሚል ዘይቤ ገልጸውት፤ ጉባዔው ለሀገር ግንባታ የሚውል አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ሰፊ ዕድል የከፈተ መሆኑን አስታውቀዋል።


የምክክር ጉባዔው ዋና ዓላማ ለዛሬ ጊዜያዊ መፍትሔ መፈለግ ብቻ ሳይሆን የቀጣዩን ትውልድ ዕጣ ፈንታ ማሳመር መሆኑን ጠቁመው "ለዛሬ ሳይሆን ለነገ ምከሩ፤ ለልጅ ልጆቻችሁ ስትሉ ምከሩ" ሲሉ አሳስበዋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

ኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ጊዜያት ይህን የመሰለ የምክክር መድረክ ባለማዘጋጀቷ በርካታ ዋጋ እንደከፈለች በማስታወስ አሁን የተገኘው ዕድል ያለፉትን ትውልዶች ነፍስ የሚያሳርፍና የሚቀጥለውን ትውልድ ደግሞ ከስህተት የሚታደግ መሆኑን አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የጽናት ምስጢር "ሽምግልና፣ ካሳና ይቅርታ" እንደሆኑ ገልጸው  በምክክሩ ሂደት ማንም ወገን ሳይገለልና ሳይጎዳ፤ አቋምን ከግል ጥቅም ይልቅ ለሀገርና ለጋራ ጥቅም ማስቀደም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።


ተሳታፊዎች ሀሳባቸውንና ልባቸውን ሰብስበው ሌላኛውን ወገን ማድመጥ እንዲችሉ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚንስትሩ "ቀፎዋን የጣለች ንብ ማር አትሰጥም፤ ማር ለመስጠት በቀፎ ውስጥ መቆየት ያስፈልጋል" በማለት መደማመጥ ለጉባዔው ስኬት ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።


ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገኙ ዕድሎችን በመጠቀም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በወታደራዊ መስኮች ውጤታማ የሪፎርም ሥራዎች መከናወናቸውን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን ውጤቶች መሰረት በማድረግ ለወደፊት የሀገሪቱን አድገት  ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ ላለፉት አራት ዓመታት እጅግ ፈታኝ የሆኑ ሂደቶችን አልፈው ጉባኤውን ለዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ያበቁትን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችና በሂደቱ ውስጥ አዎንታዊ ሚና የነበራቸውን አካላትን በሙሉ መንግሥት ማመስገኑን ገልጸዋል።


ለአራት ተከታታይ ዓመታት በርካታ የዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የታሪካዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2018 . በይፋ አስጀምሯል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

52 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።