ኢትዮጵያ በዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነት እ.አ.አ በ2025 ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ኢንተርፖል አዲስ ባወጣው የሳይበር ስጋት ግምገማ ሪፖርት አመላክቷል።
ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በ2025 ከተመዘገቡት የዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቶች 3.3 በመቶ የሚሆነውን የምትሸፍን ሲሆን ይህም ፈጣን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞዋ ከሳይበር ደህንነት መከላከያ እና ተቋማዊ ዝግጁነት ጋር አለመጣጣሙ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም እ.አ.አ 2025 በአፍሪካ ላይ የተፈፀመዉ የሳይበር ወንጀል ከ55 በመቶ በላይ የሚሆነው ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (ኤ.አይ) ጋር የተገናኘ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በአፍሪካ የሳይበር ወንጀል ያስከተለው ቀጥተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ 5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የደረሰ ሲሆን፤ ለሳይበር ደህንነት የወጣው ወጪ ደግሞ 15.3 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
የተመዘገበው የገንዘብ ኪሳራ ከ192 ሚሊዮን ዶላር ወደ 484 ሚሊዮን ዶላር ከእጥፍ በላይ ማደጉን ሪፖርቱ አሳይቷል። እንዲሁም የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ አካላት ቁጥር ደግሞ ከ35,000 ወደ 87,000 ማሻቀቡን አካቷል።
ከ36 የአፍሪካ አባል ሀገራት እና እንደ ሻዶሰርቨር ፋውንዴሽን ካሉ ድርጅቶች በተሰበሰበ መረጃ ላይ በመመስረት አጠቃላይ ግምገማው ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት ከሳይበር ደህንነት መከላከያዎች እና ከተቋማዊ ዝግጁነት በልጦ እየመጣ መሆኑን አመልክቷል።
ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ካሉት የቦትኔት (botnet) ኖዶች 1.36 በመቶውን የምታስተናግድ ሲሆን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሚታገዝ የዲጂታል ማጭበርበር ድርጊቶችም እያደገ የመጣ ማህበራዊ ስጋት መሆኑ ተጠቅሷል።
እንደ ዘመናዊ ያልሆኑ (unpatched) ሶፍትዌሮች፣ ክፍት የሆኑ ቪፒኤኖች (VPNs) እና በአግባቡ ያልተዋቀሩ የሰነድ ማኔጅመንት ሲስተሞች ዋና ዋና የጥቃት መንስዔዎች ናቸው ተብሏል።
ኢንተርፖል በ2025 በ አፍሪካ 1.1 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ የሞባይል ተጠቃሚዎች መኖራቸው እንደተመዘገበ በመግለፅ የአፍሪካ የዲጂታል እድገትም በተመሳሳይ እያደገ ነው ያለ ሲሆን የሳይበር ወንጀል ሕጎች ወጥ አለመሆናቸዉ ና የሕግ አስፈጻሚ አካላት ለኤ.አይ. ያለቸዉ ዝግጁነት በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ነው።
ይህም ሁኔታ የገንዘብ ማጭበርበርን ለመዋጋት አደገኛ የሆኑ ክፍተቶችን መፈጠራቸው በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል።በተጨማሪም የሞባይል ገንዘብ ማጭበርበር በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋ ማጭበርበር ሆኖ ብቅ ብሏል ያለ ሲሆን 97 በመቶ የሚሆኑት አገሮች ሪፖርት አድርገዋል ሲልም አክሏል።
ሌላኛው ዲጂታል ሴክስቶርሽን ሲሆን በኤአይ የሰውን ምስል በመፈብረክ ማስፈራራት ሲሆን በዚህም በአህጉሪቱ 600 ሺህ የዚህ ጥቃቶች የተመዘገቡ ሲሆን እትሂኦፒአ 8 በመቶ የሚሆነውን እንደምትሸፍን ተካቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሜታ ሜታ በ2025 ከኢንስታግራም እና ፌስቡክ 635,000 አካውንቶችን ማስወገዱ በሪፖርቱ ተገልጿል።
በኢንተርፖል ግምገማ መሰረት 94 በመቶ የሚሆኑት በቂ የዲጂታል ፎረንሲክስ መሳሪያዎች የሏቸውም። 78 በመቶ የሚሆኑት በቂ በጀት እና የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት ያለባቸው ሲሆን 89 በመቶ የሚሆኑት የድንበር ተሻጋሪ ትብብር ማነስ ዋና ማነቆ እንደሆነባቸው ገልጸዋል።
በሪፖርቱ ውስጥ ኢንተርፖል ደረጃውን የጠበቀ ዲጂታል የፎረንሲክ አቅም፣ የድንበር ተሻጋሪ ትብብር ማጠናከር፣ በሕግ አስፈጻሚ አካላት መካከል የኤ.አይ. እውቀት ላይ ኢንቨስት ማድረግና ውጤታማ መከላከል፣ መለየት እና ምላሽ መስጠትን ለመደገፍ መደበኛ የመንግስትና -የግል ትብብሮች እንዲፈጠሩ ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያ በዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቷ ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የኢንተርፖል ሪፖርት አመላከተ
አጋራ፦
እ.አ.አ 2025 በአፍሪካ ላይ የተፈፀመዉ የሳይበር ወንጀል ከ55 በመቶ በላይ የሚሆነው ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (ኤ.አይ) ጋር የተገናኘ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ተዛማጅ ጽሁፎች
ዜና
አሜሪካ በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ የኩባንያዎቿ ተሳትፎ እንዲጠናከር ጥረት እያደረገች ነው ተባለ ተባለ
ዜና
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2018 በጀት ዓመት 9.1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
ዜና
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በ62 አመራሮችና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ወሰደ
ዜና
ከ6 እስከ 7 ዓመታት ተጓትቶ የነበረው የቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ወደ ሥራ ገባ
ዜና
ሳዑዲ አረቢያ በህገ ወጥ መንገድ ዕፅ ለማዘዋወር የሞከሩ ሶስት ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር አዋለች
ዜና