Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

በመዲናዋ የትራፊክ ፖሊሶች ካሜራ ሊታጠቁ ነው

BS Bethelhem Solomon Aug 13, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 158 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
በመዲናዋ የትራፊክ ፖሊሶች ካሜራ ሊታጠቁ ነው

በተያዘው ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች መመዝገባቸውም ተገልጿል።


በአዲስ
አበባ ከተማ በትራፊክ ፖሊሶች እና በአሽከርካሪዎች መካከል የሚታዩ የሥነ-ምግባር ችግሮችን ለመቅረፍ እና የተጠያቂነት አሠራርን በቴክኖሎጂ ለማጠናከር የትራፊክ ፖሊሶች የሰውነት ካሜራዎችን እና የተሽከርካሪ ካሜራዎችን ሊታጠቁ መሆኑ ተገለጸ።

                   

በተያዘው ዓመት 1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች መመዝገባቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥር ዋና መምሪያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ምክትል መምሪያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር የሆኑት ሰለሞን አዳነ አብራርተዋል።


ተቋሙ በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የሚታዩ ክፍተቶችን በቴክኖሎጂ ታግዞ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው የትራፊክ ፖሊሶች የሚታጠቋቸው የሰውነት ካሜራዎች እና በተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠሙ ካሜራዎች ከአሽከርካሪዎች ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ከማዕከል በቀጥታ ለመከታተልና የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንደሚያስችሉ ገልጸዋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

 

ይህንኑ አሠራር አስመልክቶ ዋና ኢንስፔክተሩ "በተለይ እንግዲህ እንደነዚህ አይነት ችግሮችንም ለመቅረፍ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመን እየሰራን ያለንባቸው ሁኔታዎች አሉ ማለት ነው። የተሽከርካሪ ካሜራዎችን የትራፊክ ፖሊስ ቦዲ ካሜራዎችን ተጠቅመን ከአሽከርካሪዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመከታተል ከማዕከል የስራ መመሪያዎችን የማስተካከያ ሂደቶችን ወይም ሁነቶችን እየተከታተልን እያረምን የሚሄድባቸው ሁኔታዎች አሉ" ብለዋል።

 

ከትራፊክ ቅጣቶች ጋር ተያይዞ ቅጣቱ "ለገቢ መሰብሰቢያ ታቅዶ የሚሰራ ነው" በሚል በአሽከርካሪዎች ዘንድ ለሚነሱ ቅሬታዎች ምላሽ የሰጡት ዋና ኢንስፔክተሩ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ እንደ ሌሎቹ የንግድ ተቋማት በጀት ተይዞለት ገቢ ለመሰብሰብ የሚሰራ ሳይሆን ዋና ዓላማው ውድ የሆኑ የዜጎችን ሕይወት ከሞት እና ከአካል ጉዳት መታደግ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በከተማዋ 900 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ ከተመዘገቡት 1.5 ሚሊዮን በላይ የሕግ ጥሰቶች መካከል 100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የቀይ መብራት ጥሶ ማለፍ መሆናቸውን አስረድተዋል።

 

አሽከርካሪዎች ሕግ ሲተላለፉ አስተምሩን እንጂ አትቅጡን እያሉ ከሚያነሱት ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች የሚያሳዩት ከግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ጎን ለጎን ጠንካራ የሕግ አፈጻጸም ቁጥጥር ሲኖር ብቻ አደጋን መቀነስ እንደሚቻል ነው ብለዋል።



የቁጥጥር እና የቅጣት አፈጻጸሙ መጠናከሩ አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ውጤት እያሳየ ይገኛል ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ 2017 . 411 የነበረው የሞት አደጋ 2018 . ወደ 382 የከባድ አደጋዎች ቁጥር ደግሞ 1,985 ወደ 1,865 ዝቅ በማለት 120 አደጋዎች ቅናሽ ማሳየቱን ጠቁመዋል።

 

በአንጻሩ ቀላል አደጋዎች 115 ወደ 735 የንብረት ጉዳቶች ደግሞ 34,084 ወደ 34,702 ከፍ ማለታቸው ተመላክቷል።በተጨማሪም አሽከርካሪዎች ነባር ሕጎችን እና የመንገድ ላይ ምልክቶችን በትክክል የማወቅ ሕጋዊ ግዴታ እንዳለባቸው ተገልጿል።

 

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

65 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።