Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር እና በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ሕጋዊ ጥቅም እንደምታስከብር ገለጸች

BS Bethelhem Solomon Oct 5, 2026 2 ደቂቃ ንባብ 11 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር እና በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ሕጋዊ ጥቅም እንደምታስከብር ገለጸች

የኢትዮጵያ ቅርብ የተባለው ድንበር ከባሕር ዳርቻው 48 ኪ.ሜ ብቻ ርቀት ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል


ኢትዮጵያ
በአባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ታሪካዊና ሕጋዊ ጥቅም እንደምታስከብር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በወጣው መግለጫ አስታውቃለች።


ዛሬ ሰኞ መስከረም 25፤ 2019 የወጣው መግለጫ ቀይ ባህር ከኢትዮጵያ ጋር በመልከዓ ምድራዊም ሆነ በታሪክም የተሳሰረ የባሕር አካል መሆኑን አመልክቷል።


መግለጫው ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ዋነኛ ምንጭ መሆኗንና በማስታወስ እና በቀይ ባሕር አካባቢ ያላት ታሪካዊና መልክዓ-ምድራዊ ቁርኝት የማይካድ ሐቅ እንደሆነ ገልጿል።


ማንኛውም ቀጣናዊ ውይይት እነዚህን መሠረታዊ እውነታዎች ያገናዘበ ሊሆን እንደሚገባ መግለጫው አጽንኦት ሰጥቷል።


ይህ የኢትዮጵያ መግለጫ የመጣው በግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ አስተናጋጅነት፤ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድ እና የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የአባይ ወንዝ እና ቀይ ባህርን የተመለከት የጋራ መግለጫ ማውጣታቸውን ተከትሎ ነው።


መስከረም 24/2019 በግብፅ የተካሄደውና አራቱ ሀገራት የተሳተፉበት አራትዮሽ የምክክር ጉባኤ የጋራ መግለጫ በቀይ ባህር ላይ የካርጎና መርከቦች የነፃ ዝውውር መብት መከበር እንዳለበት ጠቅሶ የቀይ ባህር አስተዳደር እና ቁጥጥር ብቸኛ ኃላፊነትና መብት ቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያሉ ሀገራት ብቻ እንደሆነ አስፍሯል።


ቀይ ባሕር እና አባይን ጨምሮ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ ተፈጻሚነት ያላቸው ዓለም አቀፍ ሕጎች እንዲከበሩም ጠይቀዋል።


ይህን ተከትሎም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ለአባይ ወንዝ አጠቃላይ የውኃ ፍሰት 85 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ እንደምታበረክት በማስታወስ የአባይ ወንዝ አጠቃቀምን እና አስተዳደርን በተመለከተ የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች እነዚህን መሠረታዊ እውነታዎች መሠረት ያደረጉ ሊሆኑ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቷል።


አክሎም “የፖለቲካ ድንበሮች ቢለዋወጡም፤ የኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ዳርቻ በ30 ማይልስ ያህል ብቻ የምትርቅ በመሆኗ ስለ ቀጣናው የባሕር ጉዳዮች እና የደህንነት መዋቅር የሚደረግ ማንኛውም ውይይት የኢትዮጵያን ሕጋዊ ጥቅም እና ዘላቂ ቁርኝት ያገናዘበ መሆን እንዳለበት” ጠቅሷል።


ፖለቲካዊ አሻጥሮች፣ የማስገደድ እርምጃዎች ወይም በቀጣናው አለመረጋጋት የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች እና በወኪሎች በኩል የሚወሰድ የትኛውም የትነኮሳ ድርጊቶች ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሕጋዊ ጥቅም፣ ሚና እና ሃላፊነት ሊቀንሱ እንደማይችሉት አረጋግጧል።



ሆኖም ኢትዮጵያ አሁንም ለሰላም እና ውይይት እና ቀጣናዊ ትብብርን ዝግጁ መሆኗን የገለጸች ሲሆን ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን፣ የግዛት አንድነት እና መሠረታዊ ብሔራዊ ጥቅሟን ለመጠበቅ ዝግጁ እንደሆነች ገልጿል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

87 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።