Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የኢኮኖሚ ባለቤትነት ማዕረጓን ተነጠቀች

BS Bethelhem Solomon Oct 16, 2026 Updated 3h ago 1 ደቂቃ ንባብ 237 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የኢኮኖሚ ባለቤትነት ማዕረጓን ተነጠቀች

ይሁን እንጂ ይህ የደረጃ ለውጥ የኬንያ ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ በበለጠ ፍጥነት አድጓል ማለት አይደለም ተብሏል።


ኢትዮጵያ
በብር መዳከም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት መቀነሱን ተከትሎ የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ባለቤትነት ማዕረጓን መነጠቋ ተገልጿል።


ኢትዮጵያ ማዕረጓን የተነጠቀችው በ2016 ዓ.ም ባደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የብር መዳከም የሀገሪቱን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) በዶላር ሲሰላ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ በማድረጉ ነው።


በዚህም ጎረቤት ሀገር ኬንያ፤ ኢትዮጵያ ለተከታታይ አምስት ዓመታት ተቆናጥጣ የቆየችውን የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የኢኮኖሚ ባለቤትነት ማዕረግ መልሳ ተቆጣጥራለች።


የኬንያ መገናኛ ብዙሃን የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሪፖርትን ጠቅሰው እንደዘገቡት የኬንያ አጠቃላይ GDP በ2025 በ13.7 በመቶ በማደግ ወደ 135.92 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።


ይህም በ2016 ከነበራት 210 ቢሊዮን ዶላር ወደ 40 በመቶ ገደማ የቀነሰውን የኢትዮጵያን 126.35 ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ እንደሆነ አመልክቷል።


በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የ9.57 ቢሊዮን ዶላር ልዩነት ኬንያን በአፍሪካ ትላልቅ ኢኮኖሚዎች ደረጃ ሰባተኛ ያስቀመጣት ሲሆን የኢትዮጵያ ደረጃ ወደ ስምንተኛ ዝቅ ብሏል።


ይሁን እንጂ ይህ የደረጃ ለውጥ የኬንያ ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ በበለጠ ፍጥነት አድጓል ማለት እንዳልሆነ የጠቀሰው ዘገባው ይልቁንም የምንዛሬ ተመን እንቅስቃሴዎች በዶላር የተሰሉ ኢኮኖሚያዊ ደረጃዎችን በመቀየር ረገድ ወሳኝ ሚና መጫወቱን ጠቅሰዋል።


ኢትዮጵያ በ2016 ዓ.ም  መጨረሻ ሐምሌ ላይ ከIMF የ4 ዓመት የተራዘመ የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ጋር በተያያዘ ማሻሻያዎች ያደረገች ሲሆን የውጭ ምንዛሬ ቁጥጥሮችን በማላላት ወደ ገበያ መር የምንዛሬ ተመን ስርዓት ተሸጋግራለች።


በወቅቱ የኢትዮጵያ ብር ከዶላር አኳያ በ30 በመቶ የተዳከመ ሲሆን በ2016 መጨረሻ ሐምሌ ላይ ባደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ GDP እንዲሁ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።


ይህም የሚሆነው አንድ ገንዘብ ዋጋውን በሚያጣበት ወቅት ኢኮኖሚው ማደጉን ቢቀጥልም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ እቃዎችና አገልግሎቶች በዶላር የሚኖራቸው እሴት በመቀነሱ ነው።


ምንም እንኳን ቅናሽ የተመዘገበ ቢሆንም በአይ.ኤም.ኤፍ መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ እውነተኛ ኢኮኖሚ (Real GDP) እ.አ.አ በ2025 በ9.2 በመቶ በማደግ ከኬንያው 4.6 በመቶ ከፍ ያለ ነው።


የኢትዮጵያ ምንዛሬ ዋጋ መቀነስ የሀገሪቷን ውጤት ዓለም አቀፍ ግምት ዝቅ ሲያደርገው፣ የኬንያ ገንዘብ መጠናከር ግን የሀገር ውስጥ ምርትን የዶላር እኩያ ከፍ አድርጎታል።


በአይ ኤም ኤፍ የኢኮኖሚ ትንበያ እንደተጠቀሰው ኬንያ መሪነቷን እንደምትቀጥል ነው። አይ.ኤም.ኤፍ ከዚህ ቀደም ኬንያ ከምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤት እንደምትሆን ትንበያውን አስቀምጦ ነበር።


BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

91 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።