Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ኢትዮጲያ

የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው ኩርሙክ ከተማን መቆጣጠሩን ገለጸ

BS Bethelhem Solomon Jul 9, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 619 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው ኩርሙክ ከተማን መቆጣጠሩን ገለጸ

ኩርሙክ ከኢትዮጵያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር በቀጥታ የምትዋሰን በመሆኗ፣ በሱዳን፣ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የየብስ ትራንስፖርት እና የወታደራዊ አቅርቦት መስመር ለመቆጣጠር እጅግ ወሳኝ ስፍራ ነች።


የሱዳን
መደበኛ የጦር ኃይሎች በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ ሰማያዊ አባይ (ብሉ ናይል) ግዛት ውስጥ የምትገኘውን እና ከኢትዮጵያ ጋር በምትካለለው ድንበር ላይ የምትገኘውን ቁልፍ እና ስትራቴጂካዊ የኩርሙክ ከተማን መልሶ መቆጣጠሩን ሱዳን ትሪቡን አስነብቧል።


ከተማዋ ለወራት ያህል የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (RSF) እና የሱዳን ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) አብደል አዚዝ አል-ሂሉ ቡድን ጥምረት በሆነው ታጣቂ ኃይል ስር ቆይታለች።


የሱዳን ጦር አራተኛ እግረኛ ክፍለ ጦር እና ልዩ ግብረ ኃይሎች በከተማዋ ዳርቻዎች ላይ ለአምስት ቀናት ያህል ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ ሲያካሂዱ ከቆዩ በኋላ ነው ረቡዕ ዕለት ወደ ከተማዋ መግባት የቻሉት።


በጦሩ የቪዲዮ መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው በዘመቻው ወቅት በታጣቂ ቡድኖቹ ላይ ከፍተኛ የሰው ኃይል እና የወታደራዊ ንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን  ታጣቂዎቹም አካባቢውን ጥለው ወደ ደቡብ አቅጣጫ መሸሻቸውን የጸጥታ ምንጮች ገልጸዋል።


ኩርሙክ ከኢትዮጵያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር በቀጥታ የምትዋሰን በመሆኗ በሱዳን፣ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የየብስ ትራንስፖርት እና የወታደራዊ አቅርቦት መስመር ለመቆጣጠር እጅግ ወሳኝ ስፍራ ነች።


ታዲያ አማጺያኑ ባለፈው መጋቢት ወር ከተማዋን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ፤ በድንበር አካባቢው ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እና የነዋሪዎች መፈናቀል አስከትሎ ነበር ይታወሳል።


የኩርሙክ ከተማ ከእጅ መውጣት RSF ታጣቂዎች ወደ መካከለኛው ሱዳን ለማድረግ ለነበረው ወታደራዊ ስምሪት ትልቅ ውድቀት መሆኑን የፖለቲካ እና የደህንነት ተንታኞች ይናገራሉ።


የከተማዋን ነጻ መውጣት ተከትሎ በሰማያዊ አባይ ግዛት ዋና ከተማ በዳማዚን ህዝባዊ ደስታ የተገለጸ ሲሆን የአካባቢው አስተዳደር በውጊያው ሳቢያ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም እና ተፈናቃዮችን ለመመለስ ኮሚቴ ማዋቀር መጀመሩን አስታውቋል።


የኩርሙክ ከተማ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ታሪክ ውስጥ በወታደራዊ ስልታዊ ጠቀሜታዋ  የምትታወቅ ቦታ ስትሆን እስከ አሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (RSF) ወገን የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።


2023 .. ጀምሮ በሱዳን የተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት እስካሁን ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ደግሞ ለአስከፊ ሰብአዊ ቀውስ እና መፈናቀል ዳርጓል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብይ አህመድ (/)  ከሰሞኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 30 መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርበው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ በሰጡበት ወቅት የሱዳንን ጉዳይ በማንሳት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ቅንጣት ታክል ስጋት እንደሌላቸው መግለጻቸው ይታወሳል።


BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

52 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።