Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

ተጠባቂው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በነገው እለት ይጀምራል

BS Bethelhem Solomon Jul 14, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 279 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ተጠባቂው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በነገው እለት ይጀምራል

በጉባኤው ላይ ከሚቀርቡ አጀንዳዎች መካከል የህገ መንግስት ማሻሻያ እንዲሁም የመንግስት አደረጃጀት እና ቅርጽ የሚገኙበት ሲሆን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ጉዳይ ብሎም የምርጫ ስርዓት ተካትተዋል።



የኢትዮጵያ
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለረጅም ጊዜ ሲያዘጋጀው የቆየውን እና የሀገሪቱን የፖለቲካና የሕዝብ ቁርሾዎች በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት ታስቦ የተዘጋጀውን ታላቅ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ነገ ሐምሌ 8 ቀን 2018 . በይፋ እንደሚጀምር ታውቋል።


ይህ
ጉባኤ ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን፤ ከአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 4,000 በላይ ተወካዮች በአዲስ አበባ ተገኝተው የሀገሪቱን እጣ ፈንታ በሚወስኑ ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ።


የኢትዮጵያ
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ታህሳስ 20 ቀን 2014 . በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ሕግ ሲሆን የኮሚሽኑ መቋቋሚያ አዋጅ ዋና ዓላማ በታሪክ፣ በፖለቲካ እና መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚታዩ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ለዘላቂ ሰላም፣ ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት መሰረት የሚሆን መግባባት መፍጠር ነው።


በመጀመሪያው
አዋጅ ኮሚሽኑ የተሰጠው የሶስት ዓመት የስራ ዘመን የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ስራውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ ባለመቻሉ የስራ ዘመኑ ሲራዘም ቆይቷል።


በመጀመሪያው የተራዘመው በየካቲት 2017 . ሲሆን ፓርላማው ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የአንድ ዓመት ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶት ነበር። በቅርቡ የካቲት 11 ቀን 2018 . ደግሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ  የስራ ዘመኑ ለሁለተኛ ጊዜ በስምንት ወር እንዲራዘም ተወስኖ ነበር።


ለሶስት ሳምንት የሚካሄደው ጉባኤው የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አርብቶ አደሩና አርሶ አደሩ፣ የንግድ ማህበረሰብ፣ የጸጥታ ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎችም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚወከሉበት ሰፊ መድረክ ነው።


ለዚህም ኮሚሽኑ ባለፉት አራት ዓመታት በሁለቱ ከተማ መስተዳደርችና 11 ክልሎች የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማወያየት እንዲሁም ከሀገር ውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጀንዳዎችን በመሰብሰብ ለዚህ ጉባኤ እንዲበቁ አድርጓል።


በጉባኤው ላይ ከሚቀርቡ አጀንዳዎች መካከል የህገ መንግስት ማሻሻያ እንዲሁም የመንግስት አደረጃጀት እና ቅርጽ የሚገኙበት ሲሆን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ጉዳይ ብሎም የምርጫ ስርዓት ተካትተዋል።


ለዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ቀደም ሲል ይፋ የተደረጉት ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ለውይይት የቀረቡ ሲሆን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ፣ የጸጥታ ተቋማት ገለልተኝነት፣ የመሬት ባለቤትነት፣ ሙስናና መልካም አስተዳደር እንዲሁም የሰላም ግንባታ ሂደቶች በዝርዝር የሚመከርባቸው ሌሎች አጀንዳዎች ናቸው።


ጉባኤተኞቹ በስምንት ቡድኖች ተከፋፍለው የሚመክሩ ሲሆን በእያንዳንዱ ቡድን 500 ተወካዮች ተካተው ውይይቱ በሰለጠነና በሀሳብ ብስለት ላይ በተመሰረተ መንገድ እንዲሄድ ለማስቻል ከየዘርፉ የተወከሉ የሙያ ባለሙያዎች ማብራሪያዎችን እየሰጡ ሂደቱን የሚመሩት ይሆናል።



የባለሙያዎቹ ዋና ሃላፊነት ተሳታፊዎች ከስሜታዊነት ወጥተው በአጀንዳዎቹ ላይ በአግባቡ እንዲመክሩና በውይይቱ ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶችን በዘዴ ለመፍታት መሆኑም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (/) በጉባኤው ዋዜማ ባስተላለፉት መልዕክት ነገ የሚጀመረው ውይይት የእኛን እና የመጪውን ትውልድ እጣ ፈንታና የወደፊት ተስፋ ሙሉ በሙሉ የሚወስን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነው ብለዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም "ዛሬ ሀገራችን የምትሻው ጠመንጃ ያነገቡ ሳይሆን በሀሳብ ብስለት፣ በእውነት፣ በዕውቀትና በጽናት ታጥቀው የተሰናዱ የሰላም ታጋዮችን ነው" በማለት ኢትዮጵያውያን በሰለጠነ ንግግርና በሰላማዊ ውይይት የገጠሙንን ፈተናዎች አልፈን እንሻገራለን ሲሉ እምነታቸውን ገልጸዋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us
BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

52 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።