Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

ኢትዮጵያ በዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቷ ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የኢንተርፖል ሪፖርት አመላከተ

BS Bethelhem Solomon Aug 5, 2026 1 ደቂቃ ንባብ 121 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ኢትዮጵያ በዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቷ ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የኢንተርፖል ሪፖርት አመላከተ

እ.አ.አ 2025 በአፍሪካ ላይ የተፈፀመዉ የሳይበር ወንጀል ከ55 በመቶ በላይ የሚሆነው ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (ኤ.አይ) ጋር የተገናኘ እንደሆነ ተጠቅሷል።


ኢትዮጵያ
በዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነት .. 2025 ከአፍሪካ 5 ደረጃ ላይ መቀመጧን ኢንተርፖል አዲስ ባወጣው የሳይበር ስጋት ግምገማ ሪፖርት አመላክቷል።


ኢትዮጵያ
በአህጉሪቱ 2025 ከተመዘገቡት የዲጂታል ጥቃት ተጋላጭነቶች 3.3 በመቶ የሚሆነውን የምትሸፍን ሲሆን ይህም ፈጣን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞዋ ከሳይበር ደህንነት መከላከያ እና ተቋማዊ ዝግጁነት ጋር አለመጣጣሙ ተገልጿል።


ከዚህ በተጨማሪም .. 2025 በአፍሪካ ላይ የተፈፀመዉ የሳይበር ወንጀል 55 በመቶ በላይ የሚሆነው ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (.አይ) ጋር የተገናኘ እንደሆነ ተጠቅሷል።


በአፍሪካ የሳይበር ወንጀል ያስከተለው ቀጥተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ 5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የደረሰ ሲሆን፤ ለሳይበር ደህንነት የወጣው ወጪ ደግሞ 15.3 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።


የተመዘገበው የገንዘብ ኪሳራ 192 ሚሊዮን ዶላር ወደ 484 ሚሊዮን ዶላር ከእጥፍ በላይ ማደጉን ሪፖርቱ አሳይቷል። እንዲሁም የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ አካላት ቁጥር ደግሞ 35,000 ወደ 87,000 ማሻቀቡን አካቷል።


36 የአፍሪካ አባል ሀገራት እና እንደ ሻዶሰርቨር ፋውንዴሽን ካሉ ድርጅቶች በተሰበሰበ መረጃ ላይ በመመስረት አጠቃላይ ግምገማው ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት ከሳይበር ደህንነት መከላከያዎች እና ከተቋማዊ ዝግጁነት በልጦ እየመጣ መሆኑን አመልክቷል።


ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ካሉት የቦትኔት (botnet) ኖዶች 1.36 በመቶውን የምታስተናግድ ሲሆን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሚታገዝ የዲጂታል ማጭበርበር ድርጊቶችም እያደገ የመጣ ማህበራዊ ስጋት መሆኑ ተጠቅሷል።


 እንደ ዘመናዊ ያልሆኑ (unpatched) ሶፍትዌሮች፣ ክፍት የሆኑ ቪፒኤኖች (VPNs) እና በአግባቡ ያልተዋቀሩ የሰነድ ማኔጅመንት ሲስተሞች ዋና ዋና የጥቃት መንስዔዎች ናቸው ተብሏል።


ኢንተርፖል 2025 አፍሪካ 1.1 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ የሞባይል ተጠቃሚዎች መኖራቸው እንደተመዘገበ በመግለፅ የአፍሪካ የዲጂታል እድገትም በተመሳሳይ እያደገ ነው ያለ ሲሆን የሳይበር ወንጀል ሕጎች ወጥ አለመሆናቸዉ የሕግ አስፈጻሚ አካላት ለኤ.አይ. ያለቸዉ ዝግጁነት በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ነው።


ይህም ሁኔታ የገንዘብ ማጭበርበርን ለመዋጋት አደገኛ የሆኑ ክፍተቶችን መፈጠራቸው በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል።በተጨማሪም የሞባይል ገንዘብ ማጭበርበር በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋ ማጭበርበር ሆኖ ብቅ ብሏል ያለ ሲሆን 97 በመቶ የሚሆኑት አገሮች ሪፖርት አድርገዋል ሲልም አክሏል።


ሌላኛው ዲጂታል ሴክስቶርሽን ሲሆን በኤአይ የሰውን ምስል በመፈብረክ ማስፈራራት ሲሆን በዚህም በአህጉሪቱ 600 ሺህ የዚህ ጥቃቶች የተመዘገቡ ሲሆን እትሂኦፒአ 8 በመቶ የሚሆነውን እንደምትሸፍን ተካቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሜታ ሜታ 2025 ከኢንስታግራም እና ፌስቡክ 635,000 አካውንቶችን ማስወገዱ በሪፖርቱ ተገልጿል።


በኢንተርፖል ግምገማ መሰረት 94 በመቶ የሚሆኑት በቂ የዲጂታል ፎረንሲክስ መሳሪያዎች የሏቸውም። 78 በመቶ የሚሆኑት በቂ በጀት እና የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት ያለባቸው ሲሆን 89 በመቶ የሚሆኑት የድንበር ተሻጋሪ ትብብር ማነስ ዋና ማነቆ እንደሆነባቸው ገልጸዋል።


በሪፖርቱ ውስጥ ኢንተርፖል ደረጃውን የጠበቀ ዲጂታል የፎረንሲክ አቅም፣ የድንበር ተሻጋሪ ትብብር ማጠናከር፣ በሕግ አስፈጻሚ አካላት መካከል የኤ.አይ. እውቀት ላይ ኢንቨስት ማድረግና ውጤታማ መከላከል፣ መለየት እና ምላሽ መስጠትን ለመደገፍ መደበኛ የመንግስትና -የግል ትብብሮች እንዲፈጠሩ ጥሪ አቅርቧል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

59 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።