Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ቢዝነስ

ኤክሳይስ ታክስ ከፋይ የሆኑ አምራች ፋብሪካዎች ላይ የክትትል ካሜራ መገጠም ተጀመረ

BS Bethelhem Solomon Aug 31, 2026 Updated 3h ago 1 ደቂቃ ንባብ 214 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ኤክሳይስ ታክስ ከፋይ የሆኑ አምራች ፋብሪካዎች ላይ የክትትል ካሜራ መገጠም ተጀመረ

መንግሥት ለዲጂታል የክትትል ሥርዓቱ ወደ 300 ሚሊዮን ብር የሚገመት በጀት መድቧል ተብሏል።



የገቢዎች
ሚኒስቴር የኤክሳይዝ ታክስ ከፋይ የሆኑ የማምረቻ ተቋማት፣ በተለይም የቢራና የታሸጉ መጠጦች ፋብሪካዎች ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የክትትል ካሜራዎችን መግጠም እንደጀመረ ተሰምቷል። 


የፌዴራል መንግሥት ለዚህ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ግምታዊ ወጪ 300 ሚሊዮን ብር የመደበ ሲሆን ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ የግብር ባለሥልጣናት ከፍተኛ ፍላጎት ካላቸው የኤክሳይስ ዕቃዎች መሰብሰብ ከሚገባቸው ገቢ ላይ ከፍተኛ ጉድለት አጋጥሟቸዋል ተብሏል



የመንግሥት ግምቶች እንደሚያሳዩት ከፍተኛ የግብር መዝለል የሚያጋጥመው በቀጣይነት ባሉ የመረጃ ክፍተቶች፣ ሪፖርት ባለመደረግ እና ሰፊ ስወራዎች ሳቢያ ሲሆን አዲሱ የክትትል ሥርዓት የማምረቻ ሂደቶችን፣ የፋብሪካ መውጫ በሮች እና የጭነት ማጓጓዣዎችን በቅጽበት እና በርቀት በመከታተል እነዚህን ክፍተቶች ለመዝጋት ያለመ ነው


በተጨማሪም  ሚኒስቴሩ በቀጥታ በማምረቻው ወለል ላይ ያልተገደበ የዲጂታል ቁጥጥር እንዲኖረው ያስችለዋል ተብሏል።

 

Advertisement
Your ad could be here — contact us

እንደ አልኮል፣ ትንባሆ እና ለስላሳ መጠጦች ያሉ እቃዎች ላይ የሚጣለው የኤክሳይስ ታክስ ወሳኝ የገቢ ምንጮች ቢሆኑም የአስተዳደር ድክመቶች እና በሀብት መዝለል መሰብሰብ የሚገባውን ገቢ እየተሰበሰበ እንዳልሆነ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።



ይህንን አዝማሚያ ለመቀልበስ መንግሥት ከቀድሞው ባህላዊ የኦዲት አሰራር ወደ አውቶማቲክ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የታክስ ተገዢነት ማስከበር ሥርዓት እየተሸጋገረ ይገኛል።

 

በዚህም ቴክኒሻኖች እና የቁጥጥር ባለሙያዎች በዋና ዋና ማምረቻ ተቋማት ውስጥ ወሳኝ በሆኑ ቦታዎች ላይ የላቁ የዲጂታል ካሜራ ሥርዓቶችን መትከል እንደጀመሩ የኢንዱስትሪ ምንጮችን ጠቅሶ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል።

 

በተጨማሪም የኤክሳይስ ማህተም አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1004/2024 እና የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1079/2025 አምራቾች እና አስመጪዎች ለሁሉም የኤክሳይስ ዕቃዎች ልዩ መለያዎችን እንዲለጥፉ ግዴታ ይጥላሉ።



ይህ ሥርዓት ባለሥልጣናት ምርትን፣ ከውጭ ማስመጣትን እና ስርጭትን ከፋብሪካው አንስቶ እስከ የመጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ ለመከታተል ያስችላቸዋል ተብሏል

 

ይህ እርምጃ በአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት (IMF) ግፊት የተጀመረው ሀገራዊ የመካከለኛ ጊዜ የገቢ ስትራቴጂ አካል ሲሆን  የኢትዮጵያ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር ያለው የግብር ምጣኔ ዝቅተኛ መሆን ለሀገሪቱ የበጀት ክፍተት እና የዕዳ ጫና እንደ ዋና ችግር ተጠቅሷል።

 

የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፈው የግብር ዓመት 1.518 ትሪሊዮን ብር መሰብሰቡን ያስታወቀ ሲሆን ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከኤክሳይዝ ግብር ብቻ 48.8 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል።


ከዚህ ውስጥ የቢራው ዘርፍ 18.49 ቢሊዮን ብር፣ ለስላሳ መጠጦች 9.6 ቢሊዮን ብር እንዲሁም የትንባሆ ምርቶች 6.69 ቢሊዮን ብር ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

80 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።