Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ቢዝነስ

የስፖርት ውርርድና ሎተሪ ድርጅቶች 199 ቢሊየን ብር አንቀሳቅሰዋል ተባለ

BS Bethelhem Solomon Sep 21, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 108 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የስፖርት ውርርድና ሎተሪ ድርጅቶች 199 ቢሊየን ብር አንቀሳቅሰዋል ተባለ

በመስኩ የሚዘዋወረው ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን በ2018 ዓ.ም መስከረም ወር ብቻ 20 ቢሊየን ብር ተንቀሳቅሷል ተብሏል።


በስፖርት
ውርርድ እና ሎተሪ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ 199 ቢሊየን ብር ማንቀሳቀሳቸውን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በኢትዮጵያ የስፖርት ውርርድና ሎተሪ ዘርፍ ላይ ያካሄደው ገለልተኛ ምርመራ አሳየ።


በምርመራው በመስኩ የሚዘዋወረው ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን 2018 . መስከረም ወር ብቻ 20 ቢሊየን ብር ተንቀሳቅሷል ተብሏል


ይህ ግዙፍ አኃዝ 2015 . አስራ ሁለት ወራት ከተንቀሳቀሰው 4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ጋር ሲነጻጸር በአራት እጥፍ ብልጫ እንዳለው የምርመራ ሪፖርቱ ያሳያል።

አገልግሎቱ በምርመራው ፈቃድ ያላቸው ኦፕሬተሮች በኮሚሽን፣ በቅጣት፣ በፈቃድ እድሳትና ለምዝገባ መክፈል የሚጠብቅባቸውን ሕጋዊ ግዴታዎች ሙሉ በሙሉ አለመወጣታቸውን አረጋግጧል።


ረቂቅ የኦዲት ሪፖርቱ ድርጅቶቹ ፈቃድ ካገኙበት ሐምሌ 2015 . ጀምሮ ፈቃዳቸው እስከታገደበት ታሕሳስ 30 ቀን 2018 . ድረስ ያሉትን አራት ዓመታት አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሸፈነ ነው።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ / ቤዛ ግርማ መረጃው ትክክል መሆኑን አረጋግጠው ምርመራው የዘርፉን ሁኔታ በማስረጃ ለመረዳትና ቀጣይ የለውጥ ሥራዎችን ለመምራት የተከናወነ መሆኑን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል።


ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አክለውም ድርጅቶቹ በአራቱ ዓመታት ውስጥ ካንቀሳቀሱት ግዙፍ ገንዘብ ላይ ለመንስት መክፈል ከሚገባቸው 30 ቢሊየን ብር ውስጥ መክፈል የቻሉት 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ብቻ መሆኑን በመጥቀስ ከፍተኛ መጠን ያለው ገቢ ሳይገኝ መቅረቱን አብራርተዋል።

Advertisement
Your ad could be here — contact us

ምንም እንኳን የስፖርት ውርርድ በመንግሥት ውሳኔ ባለፈው ዓመት ታሕሳስ ወር ላይ ታግዶ ድርጅቶችም ፈቃዳቸው የታገደ ቢሆንም ውርርዱ አሁንም በሕገ ወጥ መንገድ መቀጠሉም ተገልጿል።


አገልግሎቱ የመጨረሻውን የኦዲት ሪፖርት እንደተቀበለ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመቀናጀት ያልተከፈለውን ገንዘብ ለማስመለስ እና በዘርፉ ሕገወጥነት ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ከዚህም በላይ የውል ስምምነቶችን ማቋረጥና ፈቃዶችን መሰረዝ ጋር ተያይዞ 100 ቢሊየን ብር በላይ የተደበቀ ገቢን በተመለከተ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተካሄደውን ምርመራ ተከትሎ የስፖርት ውርርድ ፈቃዶች የተሰረዙ ሲሆን ያልተሟሉ የውል አፈጻጸሞች በመኖራቸውም ከዲጂታል ሎተሪ ጋር የተያያዘው የግል አጋርነት ስምምነት መቋረጡ ተገልጿል።


በተጨማሪም የመንግሥት ዋና አቅጣጫ የመንግሥትን ገቢ ማስከበር፣ የተጫዋቾችን መብት ማስጠበቅና ዘርፉን በግልጽነትና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ ማድረግ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የስፖርት ውርርድና የዲጂታል ሎተሪ አገልግሎቶች በጠንካራ ቁጥጥርና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘው በአዲስ መልክ ዳግም እንዲጀምሩ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

83 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።