Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

የኢትዮጵያውያን ህይወት ዋጋ የሌለው ያስመሰለው የሳውዲ ፍርድቤቶች ውሳኔ

BS Bethelhem Solomon Jul 3, 2026 Updated 7h ago 3 ደቂቃ ንባብ 746 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
የኢትዮጵያውያን ህይወት ዋጋ የሌለው ያስመሰለው የሳውዲ ፍርድቤቶች ውሳኔ

ሳውዲ አረቢያ በዚህ ዓመት ብቻ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችን የገደለች ሲሆን፤አብዛኞቹ በአደንዛዥ ዕፅ ወንጀል የተከሰሱ የውጭ ዜጎች ናቸው።



በሳውዲ
አረቢያው የካሚስ ሙሻይት ማረሚያ ቤት በእያንዳንዱ  የሰዓት ቆጠራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች  የሞት ፍርድን በአሰቃቂ ስጋት ውስጥ ሆነው ይጠባበቃሉ።ለእነዚህ ወጣቶች የጥበቃ ኃይሎች በሩን የሚያንኳኩበት ድምፅ የመጨረሻው የሕይወት ፍጻሜያቸው  መጥሪያ ሁኖ ይሰማቸዋል።


ባለፈው ሚያዝያ ወር በአሴር ግዛት በሚገኘው በዚህ በተጨናነቀ እስር ቤት የጥበቃ ኃይሎች በችኮላ ገብተው የተወሰኑ ኢትዮጵያውያንን ስም ከጠሩ በኋላ አውጥተው እንደወሰዷቸው ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ አንድ እስረኛ ሚድል ኢስት አይ ተናግሯል። ከሁለት ሰዓታት በኋላ ግን  ሦስት ወጣቶች አንገታቸው ተቀልቶ መገደላቸውን ብሎም ለቀሪዎቹ እስረኞች ማስጠንቀቂያ እንዲሆናቸው በግልጽ እንደተነገራቸው ገልጿል።


"ጠባቂዎቹ በሩን በነኩ ቁጥር፤ ስማችን ይጠራል እና እኛም እንደ ብዙዎቹ በግፍ በተከሰሱ ሰዎች ቁጥር ውስጥ እንገባለን ብለን እንሰጋለን" ያለው በድብቅ በገባ ስልክ አማካኝነት የተናገረው እስረኛው ነው። በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን  በየመን እና ሳውዲ ድንበር ላይ ባለው ራጎ በተባለ ስፍራ ሲያዙ በአካል የደረሰባቸው ድብደባ እጅግ አሰቃቂ እንደነበር ይገልጻሉ።


Advertisement
Your ad could be here — contact us

"41 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ ሰጡኝና የእኔ እንደሆነ እንዳምን አስገደዱኝ፤ በዚያ ላይ ምን እንደሚል እንኳን የማላውቀውን ሰነድ በግድ አስፈረሙኝ" ሲል የደረሰበትን በደል ሌላኛው እስረኛ ተናግሯል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው ከቋንቋ እውቀት ውጪ በዐረብኛ በተጻፈ ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ መገደዳቸውና ምንም ዓይነት አስተርጓሚ ሳይኖር ለፍርድ መቅረባቸውን ብሎም የፍትህ ሂደቱ ፍጹም አድልዎ የተሞላበት መሆኑን አረጋግጠዋል።


እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ ከሆነ ሳውዲ አረቢያ በዚህ ዓመት ብቻ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችን የገደለች ሲሆን፤አብዛኞቹ በአደንዛዥ ዕፅ ወንጀል የተከሰሱ የውጭ ዜጎች ናቸው። በካሚስ ሙሻይት እስር ቤት ብቻ ቢያንስ 63 ኢትዮጵያውያን በአስቸኳይ የሞት ፍርድ አደጋ ላይ መሆናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ሆኗል።


በሚያዝያ ወር ከተገደሉት ዜጎች መካከል 30 ዓመቱ ክብሮም ገብረማርያም አንዱ ሲሆን ወላጆቹ የልጃቸውን ሰርግ ለማየት በጉጉት ሲጠባበቁ የሞቱዜና እንደሰሙ ሚድል ኢስት አይ ተናግረዋል። ሕገ-ወጥ ስደት ልጆቻችንን ነጠቀን የምትለው እናቱ እናቱ ግምጃ ገብረማርያም ግድያው ለእኛ ያልተዘጋ ቁስል ሆኗል ስትል ሃዘኗን ገልጻለች።



አባቱ
ገብረማርያም ገብረእግዚያብሔር በበኩላቸው ልጃቸውን መቅበር አለመቻላቸው እና የልጃቸው ሞት የህይወታቸውን አንድ ክፍል እንደቀጠፈው ይሰማቸዋል።ልክ እንደ ክብሮም ሁሉ ሌላኛው ተጎጂ ጽጋቡ ሐጎስም ለቤተሰቡ ብርሃን ለመሆን የሄደ ወጣት የነበረ ሲሆን ወላጆቹ ልጃቸው ንጹህ እንደነበር እና የተሻለ ሕይወት ለመኖር እንደተመኘ በምሬት ተናግረዋል።


የፖለቲካ አለመረጋጋት የጦርነት ጠባሳ እና የኢኮኖሚ ውድመት ኢትዮጵያውያንን ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚገፋ ዋና ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል። የክብሮም እህት ማሾ ሐጎስ የወንድሟን መገደል እያወቀች እንኳን  ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ምክንያት ለስደት እንደምትዘጋጅ ተናግራለች

የትግራይ ክልል አመራሮች እና የሃይማኖት አባቶች የሳውዲ መንግስት ሰብዓዊነትን እንዲያሳይ እና ግድያው እንዲቆም ጥሪ እያቀረቡ ሲሆን የሂዩማን ራይትስ ዋች ተመራማሪ ናዲያ ሃርድማን የሳውዲ አረቢያ አጋሮች በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል።

የክብሮም አባት አሁንም የልጃቸውን መሞት እያሰቡ ሌሎች ወላጆች ተመሳሳይ እጣ እንዳይገጥማቸው ይጸልያሉ። "ይህ ማቆም አለበት" ሲሉ በደከመ ድምፅ የተናገሩት አቤቱታ በሳውዲ እስር ቤቶች እየታፈነ ላለው የበርካታ ኢትዮጵያውያን የፍትህ ጥያቄ ተምሳሌት ሆኗል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

52 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።