Gebeya Media 💧
Loading…
Gebeya Media
Advertisement
ዜና

ከ6 እስከ 7 ዓመታት ተጓትቶ የነበረው የቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ወደ ሥራ ገባ

BS Bethelhem Solomon Jul 27, 2026 Updated 3h ago 2 ደቂቃ ንባብ 32 እይታዎች 0 አስተያየቶች
አጋራ፦
ከ6 እስከ 7 ዓመታት ተጓትቶ የነበረው የቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ወደ ሥራ ገባ

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆን ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ የፋይናንስ ፓኬጅ መዘጋጀቱን ኩባንያው ያስታወቀ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት 17 በመቶ ድርሻ እንዳለውም ገልጿል።


በኢትዮጵያ ኦሮሚያ
ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውና 330 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ይፋዊ የግንባታ ሥራውን መጀመሩ ተገልጿል።


በዓመት በአማካይ 166 ሺህ ኦውንስ ወርቅ ያመርታል ተብሎ የሚጠበቀው የኬፊ ጎልድ ኤንድ ኮፐር ኩባንያ 'የቱሉ ካፒ' የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት በጸጥታ እና ጂኦፖለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት 6 እስከ 7 ዓመታት ገደማ ተጓትቶ እንደነበር ተገልጿል።


400 ሚሊዮን ዶላር በላይ የፋይናንስ ፓኬጅ የተመደበለት ፕሮጄክቱ የኢትዮጵያ መንግስት 20 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት 17 በመቶ ድርሻ ይዟል ተብሏል።


ማዕድን ማውጣቱ ክፍት እና ከመሬት በታች የማውጣት ዘዴዎችን አጣምሮ የሚጠቀም ሲሆን 2027 መገባደጃ ላይ ስራ ጀምሮ 2028 ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።


KEFI ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሃሪ አናኖስታራስ-አዳምስ የቱሉ ካፒ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ የስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ነው ያሉ ሲሆን በቀጣዩ አስር ዓመት የማዕድን ዘርፉ ለሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በአሁኑ ወቅት ካለበት 1 በመቶ ወደ 10 በመቶ ከፍ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ዋናውን ሚና ይጫወታል ብለዋል።


እንደዘገባው ከሆነ ፕሮጄክቱ .. 2013 KEFI 75 በመቶ ድርሻውን ከኒዮታ ሚነራልስ (’Nyota Minerals’) የገዛው ቢሆንም 2014 የቀረውን ድርሻ በመግዛት የፕሮጀክቱን 100% ባለቤትነት ተቆጣጥሯል።


2015 በወቅቱ ዝቅተኛ በነበረው የወርቅ ዋጋ መሠረት የተሻሻለ የአካባቢና የኢኮኖሚ ጥናት ከተካሄደ በኋላ የማዕድን ማውጣት ፈቃድ ተሰጥቷል።


ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት በነበሩት የጸጥታና የጂኦፖለቲካዊ ቀውሶች እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ ፈተናዎች ለፕሮጄክቱ መዘግየት ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል።


ሆኖም አሁን ላይ የገንዘብ ድጋፉ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና የኢትዮጵያ መንግሥት በየደረጃው ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ኩባንያው በመግለጽ በቅርቡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር / ዐቢይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት የመሠረት ማስቀመጣቸውን አውስቷል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅቱ ፕሮጀክቱ በመንግሥትና በግል ኢንቨስተሮች ትብብር የሚሰራ መሆኑን በመጥቀስየቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ ነውሲሉ ገልጸዉታል።


ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆን 400 ሚሊዮን ዶላር በላይ የፋይናንስ ፓኬጅ መዘጋጀቱን ኩባንያው ያስታወቀ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት 17 በመቶ ድርሻ እንዳለውም ገልጿል።


ዋና ስራ አስፈጻሚው አናኖስታራስ-አዳምስ ኢትዮጵያ በቱሉ ካፒ እና በኩርሙክ ፕሮጀክቶች ላይ በመመስረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ የወርቅ አምራች ሀገር ሆና የመውጣት ትልቅ ዕድል አላት ማለታቸውን ማይኒንግ ሪቪው አፍሪካ ዘግቧል።

BS
ስለ ጸሐፊው

Bethelhem Solomon

52 ጽሁፎች
ሁሉንም ጽሁፎቻቸውን ይመልከቱ →

ተዛማጅ ጽሁፎች

አስተያየቶች (0)

አስተያየቶች ከመታተማቸው በፊት ይገመገማሉ።

አስተያየት በመስጠት የእኛን የአጠቃቀም ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ ተቀብለዋል ማለት ነው።